አስማት የተደረገበት ነቢይ?
የመሐመድ ሳይኮሎጂያዊና መንፈሳዊ አለመረጋጋት ምርመራ
David Wood
ትርጉምና ቅንበር በአዘጋጁ
የእስልምና ተቀባይነት ጥብቅ የሆነ ግንኙነት የሚኖረው ከመሐመድ ታማኝነት ጋር ነው፡፡ ማለትም መሐመድ የእግዚአብሔር መልእክተኛ መሆኑን የሚያስረዱ አሳማኝ ማስረጃዎች ካሉ፣ እኛ በትክክል እስልምና እውነት ነው ልንል እንችላለን፡፡ ይሁን እንጂ የመሐመድን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስጥሉ ጠንካራ ምክንያቶች ካሉ እስልምና እራሱን ያፈርሳል ማለት ነው፡፡
ጥንታዊዎቹ የሙስሊም ጽሑፎችና ባህሎች ቁርአንን፤ የኢብን ኢሻቅ ሲራት ራሱል- አላህን፤ የሳሂህ አል-ቡካሪን እና የሙስሊም ሳሂህን ጨምሮ የተቀናበሩት ማስረጃዎች መሐመድን እንደ ነቢይ እንዳንቀበለው እጅግ በጣም ብዙ ማስረጃዎችን ይሰጡናል፡፡ የመጀመሪያዎቹ የሰነድ ምንጮች እንደሚያሳዩት ከሆነ መሐመድ፣ የሰድቡትና ይቃወሙት ለነበሩት ብዙውን ጊዜ ረባሽና እንዲሁም እጅግ ክፉ የሆነ ግፈኛ እንደነበረ ነው፡፡ ይህም፡- በቁርአን ውስጥ ያሉ መገለጦችን ለመተላለፍ ሌላ መገለጥን እንደተቀበለ በተናገረው ላይ፣ እንዲሁም በሴቶች ላይ ስላለው የንቀት አመለካከት፣ በሴቶች ላይ ዓመፅን በመፍቀዱ፣ በባሪያ ንግድ ላይ በመሠማራቱ፣ ከዘጠኝ ዓመት ልጅ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት በማድረጉ፤ (ለእነዚህ ሁሉ እውነቶች ‹እስላም ቢሄድድ› የሚለውን ጽሑፍ ያንብቡ) እንዲሁም ለሰላም ከሆነ መዋሸት የተፈቀደ (ተቀባይነት አለው) ነው ብሎ በማወጁ ጭምር ላይ ሌሎች ሰዎች ጥያቄን በማንሳታቸው ላይ ነው፡፡ ይህም መሐመድ መልእክቱን በሚያስተላልፍበት ጊዜ ይህንን መርሆ ምን ያህል እንደተጠቀመበት ማስተዋል የሚያስደንቀን ነገር ነው የሚሆነው፡፡
ከዚህ ሁሉ ነገር በተጨማሪ መሐመድ ከአዕምሮ ሕመም ወይንም ከሰይጣናዊ ተፅዕኖ የተነሳ ይሰቃይ እንደነበረ ለመገመት (ለመጠርጠር) የሚያስችለን ምክንያት አለን፡፡ ቀደም ስላለው የሕይወቱ ታሪክ ያለው ማስረጃ (ዘገባ) እንደሚያመለከተው ከሆነ፤ እሱ ወደ እስልምና እምነት ከመቀየሩ በፊት፤ በተቀየረበት ጊዜ እና ከተቀየረ በኋላ ሳይኮሎጂያዊ ወይንም መንፈሳዊ መረጋጋት እንዳልነበረው ነው፡፡ እነዚህ አለመረጋጋቶች ከሌሎችና በመሐመድ ሕይወት ዙሪያ ካሉ እውነቶች ጋር ሲደመሩ የሙስሊም እምነት ተከራካሪዎች፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሆኑትን ብዙ ሚሊዮን ሙስሊሞችን እምነቱ እንዴት ትክክለኛና ምክንያታዊ ነው ብለው እንዳሳመኗቸው መገመት ያዳግታል፡፡
መሐመድ የአዕምሮ ችግር እንደነበረው የሚናገሩ ማስረጃዎች እስከ ልጅነቱ የኋላ ታሪክ ድረስ ይሄዳሉ፡፡ ወላጆቹ የሞቱት እሱ ወጣት እያለ ነበር፣ ስለዚህም እሱ ያደገው በአያቱና በአጎቱ ነበር፡፡ እናቱ ከመሞቷ በፊትም የምትንከባከበው ሞግዚት ነበረችው፡፡ ይህችም ሞግዚት በመሐመድ የልጅነት ጊዜ ውስጥ ስለሆኑት ያልተለመዱ ነገሮች የሚከተሉትን አያይዛ ትናገራለች፡-
‹ከተመለስን ከጥቂት ወራት በኋላ (መሐመድ) እና ወንድሙ ከድንኳኑ ጀርባ የበግ ግልገሎቻችን ጋር ነበሩ፡፡ በዚያን ጊዜ ወንድሙ ሮጦ መጣና የሚከተለውን ነገረን፡- ‹ሁለት ሰዎች ነጭ ልብስን ለብሰው ኩራይሺውን የኔን ወንድም ያዙትና ጣሉት ከዚያም ሆዱን ከፈቱና አመሰቃቀሉት›፡፡ እኛም ወደ እሱ ሮጠን ሄድን እና እሱንም ቆሞና ፊቱም ከሰል መስሎ አገኘነው፡፡ እሱንም ይዘን ምንድነው ነገሩ ብለን ጠየቅነው፡፡ እሱም፡ ‹ሁለት ነጭ ልብስን የለበሱ ሰዎች መጥተው ጣሉኝና ሆዴን ከፍተው ውስጤን በረበሩት ምን እንደሆነ አላውቅም›› አለን፡፡›
‹ስለዚህም ወደ ድንኳናችን ወሰድነው፡፡ አባቱ እንዲህ አለኝ፡ ‹እኔ የምፈራው ይህ ልጅ የልብ ድካም አለው ብዬ ነው ስለዚህም ውጤቱ ከመታየቱ በፊት ወደ ቤተሰቡ ውሰጅው አለኝ›፡፡ ስለዚህም አንስተን ወደ እናቱ ወሰድነው እሷም እኔ እንደዚያ የእሱን ደህንነት እየጓጓሁኝና ከእኔ ጋርም ልጠብቀው እየፈለግሁ እያለሁ ለምን እንደመለስነው ጠየቀችን፡፡ እኔም መልሼ ‹እግዚአብሔር እስካሁን ልጄን በጤንነት ጠብቆታል እኔም የሚገባኝን ተግባሬን እስካሁን ተወጥቻለሁ፡፡ ያመው እንደሆን ብዬ ስለፈራሁ እንደምትፈልጊው ወደ አንቺ እንደገና አምጥቼዋለሁኝ›፡፡ እሷም ምን እንደሆነ እስክነግራት ድረስ እረፍት አሳጥታ ትጠይቀኝ ነበር፡፡ እሷም ሰይጣን ይዞታል ብዬ እፈራ እንደሆነ በጠየቀችኝ ጊዜ አዎን አልኳት፡፡›
መሐመድ በሰይጣን ተይዞ እንደሆነ ትፈራ የነበረችው ሞግዚቱ ብቻ አልነበረችም፤ እራሱም ነበዩ በተመሳሳይ መደምደሚያ ላይ መጥቶ ነበር ይህም ከመልአኩ ገብርኤል መገለጥን መቀበል በጀመረበት ጊዜ ነበር፡፡ መሐመድ ከገብርኤል ጋር አድርጎት የነበረው ግንኙነት ሙሉ ገለጣ በሲራት ራሱል አላህ ላይ ይገኛል፡-
‹እግዚአብሔር በራሱ ሚሽን (ተልእኮ) ባከበረውና ለባርያው ምህረትን ባሳየበት ምሽት በሆነ ጊዜ፤ ገብርኤል ወደ እርሱ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ አመጣለት፡ ‹ወደ እኔ መጣ› አለ የእግዚአብሔር ሐዋርያም አለ፡ ‹ወደ እኔ መጣ› ‹እኔ ተኝቼ በነበረበት ጊዜ አንድ ጽሑፍ ያለበት የአልጋ ልብስ ከመሰለ ጨርቅ ጋር ሆኖ እንዲህ አለኝ፡ ‹አንብብ!› እኔም ‹ምን ላንብብ?› አልኩኝ፡፡ እሱም በዚያው ነገር በጣም አጥብቆ ተጫነኝ እኔም ሞት ነው ብዬ አስቤ ነበር እሱም ለቀቀኝና እንዲህ አለኝ ‹አንብብ!› እኔም ‹ምን ላንብብ?› አልኩኝ እሱም እንደገና በዚያው ነገር በጣም አጥብቆ ተጫነኝ ስለዚህም እኔ ሞት ነው ብዬ አሰቤ ነበር፡፡ እሱም እንደገና ለቀቀኝና ‹አንብብ› አለኝ እኔም ‹ምን ላንብብ?› አልኩኝ፡፡ እሱም በዚያው ነገር ተጫነኝና እኔም ለሦስተኛ ጊዜ ሞት ነው ብዬ ነበር እሱም ‹አንብብ› አለኝ እኔም ‹ታዲያ ምንድነው የማነበው?› አልኩኝ ይህንንም የተናገርኩት እራሴን ከእጁ ለማስመለጥ ብዬ ነው ይህንንም እንደገና እንዳያደርግብኝ ብዬ ነበር፡፡ እሱም አለኝ፡- ‹በፈጠረህ በጌታህ ስም አንብብ፤ ከረጋ ደም ሰውን በፈጠረው፤ አንብብ! ጌታህ በጣም ርኅሩኅ ነው በብዕር ባስተማረው፣ ለሰዎች ያልታወቀውን ያስተማረው› ስለዚህም እኔም አነበብኩት እሱም ከእኔ ተለየኝ፡፡ እኔም ከእንቅልፌ ነቃሁኝ ነገሩም እነዚያ ቃላቶች ልክ በልቤ ላይ እንደተጻፉ ሆነው ነበር›፡፡ Ibn Ishaq, Sirat Rasul Allah (The Life of Muhammad), A. Guillaume, tr. (New York: Oxford University Press, 1980), p. 106.
ገብርኤል መልእክቱን ወደ መሐመድ ካመጣበት የዓመፅ መንገድ በስተቀር ነገሮች ሁሉ እስካሁን ጥሩ ይመስላሉ፡፡ ነገር ግን መሐመድ ሁኔታዎቹን የተረጎመባቸው አተረጓጎም እጅግ በጣም ገላጭ ነገር ነው፡፡ ከዚህ ሁኔታ ጋር የእሱ ከገብርኤል ጋር የመጀመሪያ ግንኙነቱን እሱ ያየው (የተሰማው) ልክ በሰይጣን እንደ መያዝ አድርጎ ነው፤ ስለዚህም በውጤቱ መሐመድ ወዲያውኑ እራሱን ለመግደል ፈለገ እንዲህም አለ፡-
‹አሁን ከእግዚአብሔር ፍጥረታት ሁሉ በሰይጣን እድተለከፈ ገጣሚ ወይንም እራሱን የሚስት ሰው ዓይነት ለእኔ የሚያስጠላኝ ምንም ነገር የለም፤ እኔ ወደ እነሱ እንኳን ለመመልከት አልችልም፡፡ ያሰብኩትም እኔ ገጣሚው ወይንም የተለከፍኩት ወዮልኝ ብዬ ነው - ኩራይሽ የሆነ ይህን ስለ እኔ በፍፁም አይናገርም! ስለዚህም እኔ ወደ ተራራ ጫፍ ላይ እወጣለሁ እራሴንም ወደ ታች በመወርወር እገድልና አርፋለሁኝ፡፡› Ibn Ishaq, Sirat Rasul Allah (The Life of Muhammad), A. Guillaume, tr. (New York: Oxford University Press, 1980), p. 106.
መሐመድ ከተራራ ጫፍ ላይ እራሱን ለመወርወር ሙከራ አድርጓል ነገር ግን በገብርኤል ተይዞ ተከልክሏል፡፡ ከዚያም ቆይቶ ምንም ተጨማሪ ራዕይ (መገለጥ) ባልመጣበት ጊዜም እንደገና እራሱን ሊገድል ሞክሯል፡፡ ነገር ግን አሁንም አንዳንድ ጊዜ ገብርኤል ሲናገረው በጣም ይፈራና ይረበሽ ነበር፤ የእሱም መገለጦች ይመስሉ የነበረው በጣም በአስጨናቂዎች ሁኔታ ውስጥ ይመጡ እንደነበረ ነው፡፡
መሐመድ አለ፡ ‹የመለኮት መገለጡ ለጥቂት ጊዜያት ዘግይቶ ነበር ነገር ግን በድንገት እኔ እየተራመድሁ እያለ ከሰማይ ድምፅን ሰማሁኝ እኔም ወደ ሰማይ ስመለከት ያስደንቃል በሂራ ዋሻ ውስጥ እያለሁ ወደ እኔ የመጣውን መልአክ አየሁት እሱም በሰማይና በምድር መካከል በወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ እኔም በእሱ በጣም ፈርቼ ነበር ስለዚህም በምድር ላይ ወደቅሁና ወደ ቤተሰቤ ተመልሼ እንዲህ አልኳቸው ሸፍኑኝ፤ ሸፍኑኝ (በብርድ ልብስ)፤ ሸፍኑኝ አልኳቸው፡፡ Sahih Al-Bukhari , Number 3238.
ካዓባም እንደገና በተገነባበት ጊዜ ነቢዩ (የእግዚአብሔር በረከት በእሱ ላይ ይሁን) እና አባስ ድንጋዮችን ሊሸከሙ ሄዱ፡፡ አባስም ለነቢዩ (የእግዚአብሔር በረከት በእሱ ላይ ይሁን) እንዲህ አለው ‹(አውልቅ) የመታጠቂያ ልብስህን በአንገትህ ላይ አድርገው ድንጋዮቹ እንዳይጎዱህ አለው፡፡› (ነገር ግን የመታጠቂያውን ልብስ እንዳወለቀ እራሱን ስቶ ምድር ላይ ወደቀ ሁለቱም ዓይኖቹ ወደ ሰማይ ያዩ ነበር፡፡ እሱም ወደ ልቡ በተመለሰ ጊዜ እንዲህ አለ፡- ‹የወገቤ መታጠቂያ፣ የወገቤ መታጠቂያ› ከዚያም በወገቡ ዙሪያ መታጠቂያውን ጨርቅ እንደገና አሰረው፡፡ Sahih Al-Bukhari , Number 3829.
የአላህ ሐዋርያ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) መገለጥ በሚመጣለት ጊዜ በቀዝቃዛ አየር ውስጥ ያልበዋል፡፡ Sahih Muslim, Abdul Hamid Siddiqi, tr., Number 5763.
አይሻ እንደዘገበችው፡ መገለጥ ወደ አላህ መልእክተኛ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) ላይ በሚመጣበት ጊዜ፤ ምንም እንኳን ቀዝቃዛ ቀንም ቢሆን ግንባሩ ያልበዋል፡፡ Sahih Muslim, Abdul Hamid Siddiqi, tr., Number 5764.
አይሻ የዘገበችው ሃሪዝ ቢን ሂሺም የአላህን ሐዋርያ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) ጠየቀው፡ እንዴት ነው መገለጥ (ዋሂ) ወደ አንተ የሚመጣው? በማለት ጠየቀው፡፡ እሱም አንዳንድ ጊዜ ወደ እኔ የሚመጣው እንደሚያቃጭል ቃጭል ደወል ነው፤ በሚያቆምበትም ጊዜ ያ ለእኔ ይዤ ለማስታወስ በጣም መጥፎ ነው (በዋሂ መልክ የተቀበልኩትን)፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ መልአክ ወደ እኔ በሰው መልክ ይመጣል (እና ይናገራል) በዚያን ጊዜም የተናገረውን ሁሉ አስታውሰዋለሁ፡፡ Sahih Muslim, Abdul Hamid Siddiqi, tr., Number 5765.
ኡባንዳ ቢን ሳሚት የዘገበው ደግሞ ዋሂ (መገለጥ) በአላህ መልእክተኛ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) በሚመጣበት ጊዜ፤ በዚያን ጊዜ ከሚሰማው ሸክም የተነሳ የፊቱ እንኳን ከለር ይቀየራል፡፡ Sahih Muslim, Abdul Hamid Siddiqi, tr., Number 5766.
የእነዚህን ሁኔታዎች ትክክለኛ ባህርይ ከታሪካዊ ሁኔታው እንዲህ ነበር በማለት ለመወሰን ባይቻልም ማስረጃው የሚያመለክተው መሐመድ መገለጡ ከእግዚአብሔር የመጣ ለመሆኑና ከሰይጣን የመጣ መገለጥ ለመሆኑ ለይቶ መናገር የማይችል እንደነበረ ነው፡፡ ይህንንም በተመለከተ፣ ማለትም መሐመድ እውነትን ከውሸት የሚለይ እንዳልነበር ከሚያሳየው እጅግ በጣም ዝነኛው ምሳሌ አንዱ አሳፋሪውና መጥፎው የሰይጣን ጥቅሶች ነው፡፡
አሁን ሐዋርያው ለሕዝቡ በጎነት ጉጉት የነበረው ሆኖ ነው የሚታየው እነሱንም እስከሚችለው ድረስ ለመሳብ እየተመኘ ነው …. ሐዋርያው የራሱ ሕዝብ ጀርባቸውን እንዳዞሩበት ባየ ጊዜ እንዲሁም እሱ አመጣሁ ከሚለው መልክት መቃቃር በገጠመው ጊዜ የናፈቀው ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ መልክት መጥቶለት ከሕዝቡ ጋር መታረቅን ነበር፡፡ ለሕዝቡ ካለው ናፍቆት የተነሳ እና ለእነሱ ካለው ጭንቀት የተነሳ ይህንን ስራውን እንቅፋት የሆነበት ነገር ቢነሳለት እጅግ ይደሰት ነበር፡፡ … ከዚያም እግዚአብሔር ‹በኮከብ በሚጠልቅበት ጊዜ ያንተ ጓድ ሳይተላለፍና ሳይታለል እና ከእራሱ ምኞት ሳይናገር› የሚልን መልክት ላከ፤ እናም እሱ ቃሉ ጋ ሲደርስ ‹ስለ አል አላት እና አል ኡዛ እና አልማናት ስለ ሦስተኛና ስሌሎች አላሰብክምን›፤ ሰይጣን በእሱ ላይ በሚያሰላስልበት ጊዜ እና ወደ እሱ ሕዝብ ለማምጣት በሚያልምበት ጊዜ በምላሱ ላይ ያስቀመጠው ‹እነዚህ የተከበሩ ናቸው ጋራኒክ (ኑሚድያን ክሬንስ) ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው›፡፡
ቁራይሾች ይህንን በሰሙበት ጊዜ እጅግ በጣም ደስ አላቸው ስለ አማልክቶቻቸውም የተናገረበት መንገድ አስደሰታቸው እና ይሰሙት ጀመር፣ አማኞቹ ግን ይዘውት የነበረው የእነሱ ነቢይ ከጌታ ዘንድ ያመጣው እውነት ነው በማለት አምነው ነበር ምንም ስህተት እንዳለበትም አላስተዋሉም፣ ምንም ከንቱ የሆነ መሳት እንዳለበት ምንም አልጠረጠሩም ነበር፣ እሱም ለመስገድ በደረሰ ጊዜ ወይንም በሱራው መጨረሻ ላይ በደረሰ ጊዜ እሱ በሚሰግድበት ጊዜ ሙስሊሞችም እራሳቸው ሰገዱ፤ ነቢያቸው ሲሰግድና ያመጣውን ሲያረጋግጥና ለትዕዛዙ ሲታዘዝ ብዙ ጣዖታት አምላኪዎች ከኩራይሽ የሆኑት እና ሌሎችም በመስጊድ ውስጥ የነበሩት የአማልክቶቻቸውን ስም መጠራት ሲሰሙ ሰገዱ ስለዚህም በመስጊድ ውስጥ የነበረው እያንዳንዱ አማኙም የማያምነውም ሁሉም ሰገደ … ከዚያም ሕዝቡ ተበተነ ቁራይሾችም ሄዱ ይህም ስለ አማልክቶቻቸው በተባለው ነገር በመደሰት ነበር፡፡ እነሱም ‹መሐመድ ስለ አማልክቶቻችን ድንቅ በሆነ መንገድ ተናገረ እያሉ ነበር እሱም ባነበበው ውስጥ እነሱ የተከበሩ ናቸው በማለት አረጋግጧል ‹ጋራኒክ› ናቸው አማላጅነታቸውም ተቀባይነት ያለው ነው በማለት ነው፡፡
ዜናው የነቢዩ ጓደኞች እስካሉበት እስከ አቢሲኒያ ድረስ ደረሰ ሪፖርትም የተደረገው ኮራይሾች እስልምናን ተቀበሉ የሚል ዜና ነበር፡፡ ከዚህም የተነሳ አንዳንድ ሰዎች ከስደት መመለስ ሲጀምሩ ሌሎች ግን ወደ ኋላ ቀሩ፡፡ ከዚያም ገብርኤል ወደ ሐዋርያው መጥቶ ‹ምንድነው ያደረግኸው መሐመድ? ለእነዚህ ሰዎች እኔ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ አንተ ያላመጣሁትን ነገር ነው ያነበብክላቸው እናም እሱ ያላለህን ነገር ነው የተናገርከው› አለው፡፡ ሐዋርያውም በምሬት አዝኖ እግዚአብሔርንም በጣም ፈርቶ ነበር፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር መገለጥን ላከ፣ እሱ - ለእሱ መሐሪ ነውና እሱን አፅናናው፣ እንዲሁም ነገሩን አቀለለውና ከእሱ በፊት የነበሩት ሐዋርያትና ነቢያትም ሁሉ የሚፈልገውን እንደፈለገ የሚመኘውንም እንደተመኘ ነገረው እናም ሰይጣን እሱ በተመኘው ነገር ላይ ገና በምላሱ ላይ እንዳለ አንድን ነገር እንደጨመረበት ነው፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ሰይጣን የሰጠውን ሐሳብ ሽሮ የራሱን ጥቅስ አፅንቷል ማለትም አንተ ልክ እንደ ሐዋርያትና ነቢያት ነህ ብሎ በመናገር ነው፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር ‹ከአንተ በፊት ሐዋርያትንም ነቢያትንም አልላክንምን ነገር ግን አንድን ነገር ሲናፍቅ ሰይጣን በናፈቀው ነገር ውስጥ የራሱን ሐሳብ ይሰጣል፡፡ ነገር ግን ሰይጣን የሰጠውን ሐሳብ እግዚአብሔር ይሽረዋል፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር የራሱን ጥቅስ ያፀናል፣ እግዚአብሔር አዋቂና ጥበበኛ ነው› Ibn Ishaq, 165-166.
ይህ ክፍል የሚያሳየው፡
1. የመሐመድ መገለጦችን መቀበል ጉዳይ የተወሰነው በእሱ በራሱ የግል ምኞት ላይ ነው፡፡
2. እሱ መገለጥን ከሰይጣን ተቀብሏል፡፡
3. ከሰይጣን የተቀበለውን መገለጥ ከአላህ የመጣ ነው ብሎ ተናግሯል፡፡
4. እሱ እና ተከታዮቹ ለመገለጡ መምጣት ክብር እራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰግደዋል እንዲሁም፣
5. ለስህተቱ የነበረው የእግዚአብሔር ምላሽ፤ ‹መሐመድ ስለ ነገሩ አትጨነቅ፡፡ ነቢያት ሁሉ ሰይጣናዊ መልክቶችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ተናግረዋል› የሚል ነበር፡፡
በእርግጥ ለመሐመድ የነበረው የእግዚአብሔር ምላሽ በቁርአን ውስጥ ተጨምሯል፡ ‹ከመልክተኛና ከነቢይም ከአንተ በፊት አንድንም አልላክንም ባነበበ (ና ዝም ባለ) ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ላይ (ማጥመሚያን ቃል) የሚጥል ቢኾን እንጅ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል ከዚያም አላህ አንቀፆቹን ያጠነክራል አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው› 22.52፡፡
ስለዚህም ሰይጣን መሐመድንም እንዲሁም ከእሱ በፊት የነበሩትንም ነቢያት እንደተገመተው፣ ሐሳባቸውን ማስቀየር ችሏል ማለት ነው፡፡ ላቢድ የተባለው አይሁዳዊው አስማተኛ ‹በነቢያቶች ማሕተም› (በመሐመድ) ላይ ቁጥጥር ማድረግን ለመለማመድ ችሎ ነበር፡፡
አይሻ (አላህ በእሷ ደስ ይበለውና) የተናገረችው፡- ‹አንድ ጊዜ ነቢዩ (የአላህ በረከትና ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) አስማት ተደርጎበት ነበር ስለዚህም ያላደረገውን ነገር እንዳደረገው አድርጎ መገመትንና ማሰብን ጀምሮ ነበር›፡፡ Sahih Al-Bukhari , Number 3175.
አይሻ (አላህ በእሷ ደስ ይበለውና) የተናገረችው፡- በአላህ መእክተኛ (የአላህ በረከትና ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) ላይ አስማት ተሰርቶ ነበር፣ ስለዚህም እሱ ግብረ ስጋ ግንኙነትን ከሚስቶቹ ጋር ሳያደርግ እንዳደረገ አድርጎ ያስብ ነበር፡፡ ከዚያም አንድ ቀን እሱ እንዲህ አለ ‹ኦ አይሻ ሰለጠየቅሁት ነገር አላህ እንዳስተማረኝ ታውቂያለሽን? ሁለት ሰዎች ወደ እኔ መጡ አንደኛው በራሴ አጠገብ ሌላው ደግሞ በእግሬ አጠገብ ተቀመጡ፡፡ በእራሴ አጠገብ የተቀመጠው በእግሬ ስር ለተቀመጠው ‹ይህንን ሰው ምን ነካው? በማለት ጠየቀው፡፡ ሁለተኛውም ‹እሱ በአስማት ቁጥጥር ውስጥ ነው ያለው አለው› የመጀመሪያውም ሰው ‹በእሱ ላይ አስማትን የሰራው ማን ነው?› አለ፡፡ ሁለተኛውም መልሶ ‹ላቢድ ቢን አል-አሳም፤ ከባኒ ዙራይክ የሆነው ሰው ነው እሱም የአይሁዶች አጋዥ እና ግብዝ ነው› በማለት መለሰ፡፡ የመጀመሪያው ‹እሱ ምን ነገርን ነው የተጠቀመው?› አለ፡፡ ሁለተኛውም ‹ማበጠሪያና በውስጡ ፀጉር የተጣበቀበት ነው› በማለት መለሰ፡፡ Sahih Al-Bukhari , Number 5765.
ኢብን ኢሻክ ደግሞ ሪፖርት ያደረገው ‹ላቢድ ቢን አሳም … የአላህን ሐዋርያ አስማት እንዳደረገበት ስለዚህም እሱ ወደ ሚስቶቹ መምጣት እንዳልቻለ› ነው፡፡ Ibn Ishaq, p. 240፡፡ ጉይላም በዚህ ላይ የጨመረው ማስታዎሻ በባህል ማስረጃ መሠረት ‹አንድ አስማት ለአንድ ዓመት እንደሚቆይ ነው› Ibn Ishaq, p. 240፡፡
ግምገማ
በጥንታዊና በጣም ታማኝ በሆኑት የሙስሊም ጽሑፎችና ልማዶች መሠረት የመሐመድ የመጀመሪያው ከመለኮት ጋር ግንኙነት የማድረጉ ጉዳይ ስሜት፣ እሱ በአጋንንት እንደተያዘ የመሰለው የነበረ መሆኑ ነው፡፡ የዚህ ልምምድ መሐመድን እጅግ በጣም እረብሾት ነበር ስለዚህም እሱ እራሱን ለመግደል ያስብ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ የኢብን ኢሻክ ታሪክ አለን ይህም የመሐመድ የመጀመሪያው የሕይወት ታሪክ ወይንም ባዮግራፊ ነው፡፡ ይህም የያዘው የነቢዩ የልጅነት ሞግዚቱ እሱ በአጋንንት እንደተያዘ (እንደተለከፈ ማሰቧን የያዘ ነው)፡፡ አንዳንዶቹ ዝርዝር የመሐመድ የመገለጥ ሁኔታዎች ይህንን እውነታ የሚደግፉ ነው የሚመስሉት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ስለመገለጦቹ እጅግ በጣም ይረበሽ ነበር፤ ስለዚህም አንድ ሰው እንዲሸፍነው በመጮኽ ይጣራ ነበር፡፡ በቀዝቃዛም ሁኔታ ውስጥ እንኳን እጅግ በጣም ያልበው እና ፊቱም ይቀያየር ነበር፡፡ በተጨማሪም መሐመድ እውነተኛ መገለጦችን ከሰይጣናዊ መገለጦች መለየት አይችልም ነበር፤ እንዲሁም ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያህል የቆየና በጠንቋዮች ቁጥጥር ስር ባደረገው አስማት ስር ሆኖ ነበር፡፡
በምዕራብ የመሐመድ ተቺዎች እሱ በሰይጣን ተይዞ ነበር የሚለውን ለመናገር ፈጣኖች ናቸው፡፡ እኛ ይህንን ለማለት የሚያስችል በቂ ማስረጃ ቢኖረንም እንኳን፤ እንዲህ ዓይነቱ መደምደሚያ ላይ መምጣት ምናልባትም በጣም መቸኮል ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ የምናውቀው ነገር በትክክል በመሐመድ በኩል አንድ የሆነ ችግር እንዳለ ነው ነገር ግን እንዲህ ያለ ችኩል የሆነ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችለን ብቁ የሆነ ማስረጃ የለንም፡፡ ይሁን እንጂ ያሉት ማስረጃዎች አንድ አስተዋይ የሆነ አዕምሮ ላለው ሰው የመሐመድን የነቢይነት ጥያቄ ታማኝነት በጣም እንዲጠራጠረው ለማድረግ በጣም በቂ ናቸው፡፡ አንድ ሰው ከሰይጣን የሆኑ ጥቅሶችን (እራሱ አምኖበት) የሰበከ እና በአስማተኞች ቁጥጥር ስር የወደቀ ሰው፤ እኔ የእግዚአብሔር ታላቅ ነቢይ ነኝ እያለ ከተናገረ ለነቢይነቱ እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ማስረጃን እስካላቀረበ ድረስ በምንም ምክንያት እምነት ሊጣልበት አይቻልም፡፡ ይህንም ማለትም ነቢይነቱን በትክክል የሚደግፍ የእስልምና ምንም ማስረጃ እስከሌለ ድረስ እኛ መሐመድ የእግዚአብሔር መልክተኛ የመሆኑን ሚና ጥያቄ ውስጥ በመጣላችን እኛ ትክክል ነው የምንሆነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ እኛ የሌላውን የእግዚአብሔርን መልእክተኛ ሕይወት፣ ማለትም የናዝሬቱ ኢየሱስን ሕይወት በምንመረምርበት ጊዜ የምናገኘው መሐመድ ሙሉ በሙሉ ተቀበይነት እንደማይኖረው ሆኖ ነው፡፡ ለምሳሌም የኢየሱስን ከሰይጣናት ጋር የነበረውን አንዱን ግንኙነት ብቻ እንኳን ተመልከቱ፡-
‹ወደ ቅፍርናሆምም ገቡ፤ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ። እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጻፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ። በዚያን ጊዜም በምኩራባቸው ርኵስ መንፈስ ያለው ሰው ነበረ፤ እርሱም። የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ፥ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ብሎ ጮኸ። ኢየሱስም። ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው። ርኵሱም መንፈስ አንፈራገጠውና በታላቅ ድምፅ ጮኾ ከእርሱ ወጣ። ሁሉም። ይህ ምንድር ነው? በሥልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው? ብለው እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ።› ማርቆስ 1.21-27፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ቁርአን ከሚናገረው በተቃራኒ መንገድ የእግዚአብሔር መልክተኞች ሁሉ አንዳንድ ጊዜ የሰይጣን መጠቀሚያ አሻንጉሊቶች አልነበሩም፡፡ ቢያንስ በሰይጣናት ኃይል ሁሉ ላይ ሙሉ የሆነ ስልጣን ያለውን አንድ እናውቃለን፡፡ እኛ የትኛውን መልእክተኛ መስማት እንደሚገባን መምረጥ የሚያስፈልገን ከሆነ (ይህም ክርስትኖችም ሙስሊሞችም ማድረግ ያለባቸው ውሳኔ ነው) በሕልውናው ብቻ ሰይጣናትን ያስፈራራ የነበረውን መታመን ብልህነት እና ማስተዋል አይሆንምን? በተጨማሪም ኢየሱስ ተከታዮቹን ያስጠነቀቀው ‹ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤› ማቴዎስ 24.11 በማለት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሁሉም የሐሰት ነቢያት ሆነ ብለው ተከታዮቻቸውን አላሳሳቱም፡፡ አንዳንዶች ይህን ያደረጉት በሰይጣን እየተመሩ ነበር፡፡ እናም ከዚህ በላይ ያየነው ማስረጃው በጣም የሚያስረዳው ነገር ቢኖር መሐመድ በዚህ መስፈርት ውስጥ እንደሆነ ነው፡፡ የራሱ ተከታዮችም እንኳን እሱ አስማት ተደርጎበት እንደበረ ይናገራሉና፡፡
የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-
ከዚህ በላይ ያለው ጽሑፍ ግልፅ እንዳደረገው ስለመሐመድ የተሰጡት ብዙዎቹ ማስረጃዎች የሚያመለክቱት እሱ በሰይጣን የተያዘ ወይንም የተለከፈ እንደነበረ ነው፡፡ በመሆኑም እንዲህ ዓይነቱ ሰው ከእግዚአብሔር አመጣሁ ያለው መልእክት በእውነት ከእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም ምክንያቱም በታሪክ ከተገለጡት እውነተኛ ነቢያት ሕይወትና ልምምድ በጣም የተለየ ነውና፡፡
ስለሆነም ስለመንፈሳዊ ሕይወትዎ እና ከእግዚአብሔር ጋር ስላለዎት የግል ግንኙነት ዛሬ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባዎታል፡፡ የምንከተለው እምነት የዘላለም ሕይወትን የሚወስን ጉዳይ እንጂ ጊዜያዊ ቡድን ውስጥ የመካተት ጉዳይ አይደለም፡፡ የእኛም ዓላማ የተደበቀውን እውነት እንድትረዱና የምትከተሉትን ሃይማኖት እንድትመረምሩ ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም እኛ በእግዚአብሔር ፀጋና እርዳታ አማካኝነት እውነተኛ እና ስህተት የሌለበትን እውነት ስለምናውቅና በዚህም እውነት ትክክለኛ የሕይወት ለውጥንና ትርጉምን ስላገኘን ጭምር ነው፡፡ ይህንንም እናንተ እንድታውቁ በእውነት ፍላጎታችንም ፀሎታችንም ነው፡፡
ለዚህ ሊረዳዎት የሚችለው ታዲያ ምንድነው? ለዚህ የሚረዳዎት መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና ከእግዚአብሔር ቃል ላይ እውነትን መረዳት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረትን ሊያደርግ የሚችለው እንዴት እንደሆነ፤ እግዚአብሔርን ሊያመልክ፤ ፀሎቱ ሊሰማ፤ የዘላለም ሕይወት ማለትም የመንግስተ ሰማይ ወራሽ ሊሆን የሚችለው እንዴት እንደሆነ የሚያስረዳ በጣም ግልፅ የሆነ መልእክት አለው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን አግኝተው ያንብቡ ለዘላለም የሚጠቅምዎት ሆኖ ያገኙታል፡፡ እግዚአብሔር ይርዳዎት፡፡
የትርጉም ምንጭ: A Bewitched Prophet? Examining Muhammad’s Psychological and Spiritual Stability by David Wood
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ