አዳዲስ መረጃዎች
መያዝያ 19፣ 2002 (27 April 2010)
በM. Rafiqul-Haqq እና በ P. Newton የተዘጋጀው ‹የሴቶች ቦታ በንፁህ እስልምና (ክፍል አራትና አምስት) › የሚለው ተከታታይ ጽሑፍ፣ እስልምና ስለ ሴቶች ያለውን አመለካከትና ስለ እምነቱም አጠቃላይ የሆነ ግንዛቤን ያካተተ ነው፡፡
መያዝያ 12፣ 2002 (20 April 2010)
በM. Rafiqul-Haqq እና በ P. Newton የተዘጋጀው ‹የሴቶች ቦታ በንፁህ እስልምና› የሚለው ተከታታይ ጽሑፍ፣ እስልምና ስለ ሴቶች ያለውን አመለካከትና ስለ እምነቱም አጠቃላይ የሆነ ግንዛቤን ያካተተ ነው፡፡
መጋቢት 12፣ 2002 (21 March 2010)
መሐመድ ለሴቶች ስላለው ዝቅተኛ አመለካከት ‹በአልጋዎቻቸው ላይ ዝጓቸው እና ደብድቧቸው› በሚለው የDavid Wood ጽሑፍ እስልምና ስለሴቶች ስላለው አመለካከት ግሩም ግንዛቤን ያስጨብጣል፡፡
የካቲት 20፣ 2002 (27 February 2010)
በሲዖል ውስጥ ካሉት ነዋሪዎች ውስጥ እጅግ በጣም አብዛኞቹ ሴቶች መሆናቸውን መሐመድ
መመልከቱን በሚገለጠው ሐዲት መሰረት ላይ የተመሰረተው ጽሑፍ ‹የሲዖል ውስጥ ነዋሪዎች ብዙዎቹ ሴቶች ናቸው›፣
በእስልምና ውስጥ ስላለው የሴቶችና የወንዶች ልዩነት አንድ ማስረጃ ነው፡፡
የእንግሊዝኛው ገፅ ‹ሴቶች በእስልምና› ክፍል ላይ የቀረበው ይህ ‹አላህ ሚስቶችን ረስቷቸዋልን?› የሚለው ጽሑፍ
በወንዶችና በሴቶች መካከል ቁርአን ስላስቀመጠው ልዩነት ያስረዳል፡፡
ጥር 29፣ 2002 (6 February 2010)
ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስንና ቁርአንን ለማወዳደር ሲሞክሩ ይታያሉ፡፡ <መጽሐፍ ቅዱስንና ቁርአንን ማወዳደር> በሚለው በዚህ አጭር ጽሑፍ ውስጥ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ከቁርአን ጋር ብቻ ማወዳደር ትክክል እንዳልሆነ Samuel Green በግልፅ አቅርቦታል፡፡
ጥር 21፣ 2002 (29 January 2010)
ቁርአን ስለ አምላክ በውስጡ ከሚሰጠው ማስረጃዎች ላይ ግልፅ ሊሆን እንደሚችለው በፍፁም ከእግዚአብሔር የመጣ ሊሆን አይችልም፣ በማለት የBassam Khoury አጭር ጽሑፍ በቁርአን 42.11 ላይ ተመስርቶ ግሩም ትንተናን ያቀርብልናል፡፡
ጥር 9፣ 2002 (17 January 2010)
መሐመድ ነቢይ ሆኖ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትንቢት እንደተተነበየ ብዙ ሙስሊሞች ሲናገሩ ይደመጣል፡፡ አብዛኛውንም ጊዜ የሚጠቀሱት ጥቅሶች የታወቁ ናቸው፡፡ በእነዚህን ጥቅሶች ላይ በመመስረት David Wood ያቀረበው ‹መሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ?› የሚለው ጽሑፍ ግሩም የሆነ ማብራሪያን ያቀርብና ብዙ ክርስትያኖች ያላስተዋሉትንና ስለ ነቢዩ መሐመድ የተገሩትን እውነተኛ ትንቢቶችን ደግሞ ገልጦ ያሳየናል፡፡
ታህሳስ 11፣ 2002 (20 December 2009)
በቁርአን 2.97 ውስጥ ያለው ዓረፍተ ነገር፣ ለሚያነበው ሁሉ አስገራሚ ነው፡፡ ጸሐፊው Jochen Katz ይህንን ጥቀስ በሎጂካዊ የቋንቋ ሕግ ትንተና መሰረት ከተነተነ በኋላ የደረሰበት መደምደሚያ ጠቃሚ ትምህርት ሰጪ ነው፡፡ <‹በላቸው› - የሚለው የተምታታ አባባል የተዘበራረቀበት የቁርአን ጸሐፊ!>ን ያንብቡ::
ህዳር 18፣ 2002 (27 November 2009)
በቁርአን ውስጥ የተጠቀሰው ‹ኢሳ› የመጽሐፍ ቅዱሱ ጌታ ኢየሱስ ነውን? ቁርአን ለ93 ጊዜ ያህል ‹ኢሳ› እያለ የሚጠራው የመጽሐፍ ቅዱሱን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ነውን? Jay Smith የጻፈው ይህ ጽሑፍ የቁራኑን ‹ኢሳ› ከመጽሐፍ ቅዱሱ ጌታ ኢየሱስ ጋር በማነፃፀር የሚያቀርበው እውነት ለእምነታችን የሚጠቅም አስገራሚ ብርሃንን ይፈነጥቃል፡፡
ህዳር 11፣ 2002 (20 November 2009)
ኦሪት ዘዳግም 18.18-19 በመጠቀም መሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ትንቢት የተነገረለት ነቢይ ነው በማለት ሙስሊሞች ይናገራሉ፡፡ በDavid Wood የተጻፈው ይህ አስገራሚ <የኦሪት ዘዳግም ምርመራዎች:...> የተሰኘ ትንተና ግን ቀጣዩም ኦሪት ዘዳግም 18.20 መታየት እንዳለበት አመልክቶ ያቀረበው ማስረጃ መሐመድ ሐሰተኛ ነቢይ እንደሆነ ነው፡፡
ቁርአን በሰማይ ካለው የመጽሐፍት እናት በመሐመድ በኩል የወረደና ምንም ስህተት እንደሌለበት ሲነገር ዘመናት አልፈዋል፡፡ ይህንን ሐሳብ አሁንም ብዙዎች ያስተጋቡታል፣ ነገሩ እውነት ነውን? የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ Jay Smith በዚህ በሁለተኛው ክፍል ነገሩ እንደተባለው ሁሉ እንዳልሆነ ከራሱ ከቁርአን የመነጩ ማስረጃንና ውጫዊ ማስረጃዎችንም ያቀርብልናል፡፡
ህዳር 5፣ 2002 (14 November 2009)
ቁርአን በሰማይ ካለው የመጽሐፍት እናት በመሐመድ በኩል የወረደና ምንም ስህተት እንደሌለበት ሲነገር ዘመናት አልፈዋል፡፡ ይህንን ሐሳብ ብዙዎች አሁንም ያስተጋቡታል፣ ነገሩ እውነት ነውን? የዚህ ተከታታይ <የቁርአን ውጪያዊና ውስጣዊ ሁኔታ ሲገመገም> የተሰኘ ጽሑፍ ጸሐፊ Jay Smith ግን ነገሩ እንደተባለው እንዳልሆነ ከራሱ ከቁርአን የመነጩ ውስጣዊ እና ደግሞም ውጫዊም ማስረጃዎችን ያቀርብልናል፡፡
የክርስትያኖችን ቅዱስ መጽሐፍ እንዲሁም ወንጌልን በተመለከተ ቁርአን የተለወጡ ወይንም የተበረዙ ናቸው በማለት በፍፁም አይናገርም፡፡ ይሁን እንጂ ስለወንጌል የተናገራቸው ገሮች ቅራኔዎች አሏቸው፣ እነዚህን ቅራኔዎች የመረመረው <ወንጌል ምን ዓይነት መጽሐፍ ነው?> በሚለው ጽሑፍ ውስጥ Jochen Katz ምጥን ያለች ግሩም መግለጫን አቅርቧል፡፡
ጥቅምት 28፣ 2002 (7 November 2009)
በቁርአን ውስጥ ያሉትን እስላማዊ ሕግጋት ለቅሞ በማውጣት M. J. Fisher, M.Div አንድ መቶ ስድስት ጥቅሶችን በዚህ <እስላማዊ ሕግ> በተሰኘው ጽሑፍ ውስጥ አቅርቦልናል፡፡ በመግቢያውም ላይ የመጽሐፍ ቅዱስንና የእስላማዊ ሕግጋትን ምንጮች በንፅፅር መልኩ ግሩም አድርጎ ጥቆማ ሰጥቷል፡፡
ጥቅምት 19፣ 2002 (29 October 2009)
የእስልምናው ቁርአን ከክርስትያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የወሰዳቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ፣ እስልምናና ክርስትና በጣም የተቀራረቡ እምነቶች ናቸው በማለት አንዳንዶች ይገምታሉ፡፡ ሁኔታውን በትክክል ለመረዳት እንድንችል M. J. Fisher, M.Div. <ክርስትናና እስልምና> በሚለው በዚህ ጽሑፍ ውስጥ መሠረታዊ ንፅፅሮችን በግሩም ሁኔታ አስቀምጦልናል፡፡
ጥቅምት 4፣ 2002 (14 October 2009)
ስለ ጦርነትና ሰላም ቁርአን በዘጠና ጥቅሶቹ ውስጥ ብዙ አስገራሚ ነገሮችን ይናገራል፡፡ ያለምንም ተጨማሪ ማብራራት M. J. Fisher, M.Div. ቁርአን ውስጥ ለቅሞ ያወጣቸው እነዚህ ጥቅሶች እራሳቸው ለራሳቸው እና ለእስልምና እምነት ብዙ ይናገራሉ፡፡ ይህን <ጦርነትና ሰላም> የተሰኘ ትርጉም ይዩ፡፡
መስከረም 20፣ 2002 (30 September 2009)
በዚህ ጽሑፍ <ነፃ ፈቃድና - የአስቀድሞ ውሳኔ> M. J. Fisher, M.Div. ቁርአን ውስጥ ያሉ ሃያ ስድስት ጥቅሶችን አስቀምጧል፡፡ ጥቅሶቹም ስለመመረጥና ስለመምረጥ፣ እንዲሁም አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ገነት ነው የሚገባው ወይንስ ሲዖል ለሚሉት የሃይማኖት ወሳኝ ትምህርቶች ምን እንደሚያቀርቡ ያሳየናል፡፡
መስከረም 12፣ 2002 (22 September 2009)
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስማቸው የተጠቀሱ ብዙ የብሉይና የአዲስ ኪዳን ሰዎች በቁርአንም ውስጥ በብዛት ተጠቅሰዋል፡፡ እንዴት ተጠቀሱ? የተጠቀሱበት ሁኔታና ታሪክ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተመሳሳይነት አለው ወይ? ትክክለኛውና እውነት የሚመስለውስ የትኛው ነው? ለሚሉት ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ለማግኘት መመርመር እንዲቻልና ወደ እውነትም ለመድረስ M. J. Fisher, M.Div. የሚያስገርሙ እውነቶችን በዚህ ጽሑፍ <መጽሐፍ ቅዱሳዊ ገፀ ባሕርያት በቁርአን> አቅርቦልናል፡፡
መስከረም 2፣ 2002 (12 September 2009)
ስለ እስልምና እምነት ጀማሪ መሐመድና ስለ ቁርአን ታሪክ ምን ያህል ታውቃላችሁ? ይህ <የመሐመድና የቁርአን ታሪክ> የተሰኘ የM. J. Fisher, M.Div ጽሑፍ እውነተኛ ማስረጃ ያላቸውን መጠነኛ ታሪካዊ እውነቶችን በግልጥ ያስነብበናል፡፡
ነሃሴ 7፣ 2001 (13 August 2009)
አንድ ሙስሊም የኃጢአት ይቅርታ እርግጠኝነትን በማግኘት የመንግስተ ሰማይ ወራሽ ሆኜአለሁ በማለት መናገር ይችላልን? ይህንንስ ለማለት እምነቱና የእምነቱ መጽሐፍ ቅርአን ይፈቅድለታልን? M. J. Fisher, M.Div. ደኅንነትን አስመልክቶ ቁርአን የሚያስተላልፈውን እውነታ በዚህ <ደኅንነት በቁርአን> በተሰኘው ጽሑፍ ውስጥ ለቅሞ አቅርቦታል፡፡
ነሃሴ 1፣ 2001 (7 August 2009)
በእስራኤልና በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ጥልቅ የሆነ ጥላቻ የመኖሩ መሠረታዊ ምክንያት ምንድነው? ለመሆኑ ሙስሊሞች አይሁዶችን አምርረው እንዲህ የሚጠሏቸው ለምንድነው? የሚሉ ጥያቄዎች በሰዎች ሁሉ አዕምሮ ውስጥ ሊጉላሉ ይችላሉ፡፡ ቁርአን አይሁዶችን በተመለከተ የሚናገሩ አዎንታዊና አሉታዊ የሆኑ ሰባ አንድ ጥቅሶችን በመልቀም የM. J. Fisher, M.Div <አይሁዶች በቁርአን> የተሰኘው ጽሑፍ መሠረታዊ የሆኑ ግንዛቤዎችን ይሰጠናል፡፡
ሓምሌ 17፣ 2001 (24 July 2009)
ትንቢትና ፍፃሜ በአንድ እምነት ዙሪያ የሚገኙ ነገሮች ናቸው፡፡ ቁርአን እንደ ሃይማኖት መጽሐፍ ትንቢቶች አሉት፣ በዓለም ውስጥ ስለሚሆኑ ክስተቶች ቁርአን የተናገረው ትንቢት የሚገኘው በአንድ ጥቅስ ላይ ብቻ ነው፡፡ M. J. Fisher, M.Div; በዚህ <የዓለም ክስተቶች ትንቢት> በተሰኘው ጽሑፍ ውስጥ የአንዱን ጥቅስ ሐሳብና የትንቢቱን ሁኔታ ያብራራል፡፡
በቁርአን ውስጥ ያሉት የወንጀለኛ መቅጫ ሕጎች ብዙ እና ጭከና የተሞላባቸው ናቸው፡፡ <በቁርአን ውስጥ የወንጀለኛ መቅጫዎች> ደግሞ Fisher አስራ ስምንት የሚሆኑትን የቁርአን ጥቅሶች አስቀምጦልናል፡
ሓምሌ 15፣ 2001 (22 July 2009)
የክርስቶስን የመስቀል ስቅለት በተመለከተ ሙስሊሞች ሁሉ ወጥ የሆነ አመለካከት የላቸውም <በኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት - የእስላም ግራ መጋባት!>፡፡ Derik Adams; The Confusion of Islam regarding the Crucifixion of Jesus Christ; በሚለው ጽሑፉ ውስጥ በቁርአን 4.157 ላይ በሙስሊም ሊቃውንት የተሰጡ ትንተናዎችንና አራት ፅንሰ-ሐሳቦችን አቅርቦልናል፡፡
ሓምሌ 10፣ 2001 (17 July 2009)
ጋብቻንና ፍቺን አስመልክቶ ሃያ አምስት የሚሆኑ ጥቅሶች በቁርአን ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ጥቅሶች M. J. Fisher, M.Div አንድ ላይ ሰብስቦ እንድናነባቸውና እንድናስብባቸው በ<ጋብቻና ፍቺ በቁርአን> አቅርቦልናል፡፡
ሓምሌ 8፣ 2001 (15 July 2009)
በRoland Clarke ከተጻፈው Lighting Up The Darkness የተቀናበረው ይህ ‹መንፈሳዊውን ጨለማ ማብራት› የሚለው ጽሑፍ አንድ ሰው መንፈሳዊ ብርሃንን ለማግኘት እንዴት እንደሚችል ያሳያል፡፡ ጌታ ኢየሱስ እራሱ እንዲሁም የሰበከው ወንጌል ብርሃን እንደሆነም በማስረጃ ያቀርባል፡፡
ሰኔ 27 ፣ 2001 (4 July 2009)
ቁርአን እጅግ በጣም አስገራሚ በሆኑ አባባሎች የተሞላ ነው፡፡ አዘጋጆቹ አስገራሚ የሚሏቸውንና ከቁርአን ውስጥ ያወጧቸውን የጥቅሶች ስብስብ (የቁርአን አስገራሚ ጥቅሶች) አቅርበዋል ፡፡ እነዚህን ጥቅሶች በማስተዋል ማንበብ ምን መከተል እንዳለብን ለማስተዋል ይጠቅማል፡፡
ሰኔ 21 ፣ 2001 (28 June 2009)
ቁርአን ስለሴቶች ምን ይናገራል? M. J. Fisher, M.Div. ባዘጋጀው በዚህ ጽሑፍ (የሴቶች ሁኔታ በቁርአን) ላይ በቁርአን ውስጥ ስለሴቶች የሚናገሩትን ሃያ ዘጠኝ ጥቅሶች በመልቀም አስቀምጧቸዋል፡፡ አንድ በአንድ እያገናዘቡ ማንበብ ስለምንከተለው እምነት ትክክለኛ ግንዛቤን እንድናገኝ ይረዳናል፡፡
የሙስሊሞቹን አላህ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ነውን? ይህንን ጥያቄ አስበውበት የሚያውቁ ከሆነ ወይንም አስቸግሮዎት የሚያውቅ ከሆነ ይህንን ጽሐፍ (አላህ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ነውን? አጠቃላይ እይታ) ማንበብ ይኖርብዎታል፡፡ በAnswering Islam ውስጥ General Reflection በሚል ርዕስ ስር የሰፈረው ይህ ጽሐፍ ግሩም እይታን ይሰጣል፡፡ ለመሆኑ የሙስሊሞች አላህ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ሊሆን እንዴት አይችልም?
ሰኔ 13 ፣ 2001 (20 June 2009)
ቁርአን የሚለው ቃል ትርጉም ‹ማስታወስ› ነው፡፡ ቁርአን በሙስሊሞች ሁሉ የተከበረ መጽሐፍ ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ (ቁርአን ባጠቃላይ ምን ያሳያል?) ጸሐፊ M.J Fisher, M.DIV ቁርአን ስለ እራሱ የሚናገረውን ነገር ከስልሳ አንድ ጥቅሶች ውስጥ በመልቀም ለአስተዋይ አንባቢዎች ግልፅ ለማድረግ ሞክሯል፡፡
ሰኔ 6 ፣ 2001 (13 June 2009)
የሙስሊሞች መጽሐፍ ማለትም ቁርአን ስለመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ነገሮችን ይናገራል፡፡ በM.J Fisher, M.DIV የተጻፈው ይህ መጽሐፍ ቅዱስ በቁርአን ውስጥ የሚለው ጽሑፍ ቁርአን ስለመጽሐፍ ቅዱስ የሚናገራቸውን ሰባ አንድ ጥቅሶች የሚጠቁምና እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡
ግንቦት 29 ፣ 2001 (6 June 2009)
ቅዱስ መጽሐፍ በተባለ አንድ መጽሐፍ ውስጥ ብዙ ተረቶችን ብታገኙ ምንድነው የምትሉት? M. J. Fisher, M.Div በቁርአን ውስጥ ያሉትን ተረቶች ለቅሞ በማውጣት Unusual Tales (ያልተለመዱ የቁርአን አባባሎች) በሚል ርዕስ ውስጥ አቅርቧቸዋል፡፡ ሙስሊም ወገኖቻችን በጥንቃቄ ተመልከቷቸውና እና የእምነታችሁን መሰረት መርምሩ፡፡
ቁርአን ስለተፈጥሮና ስለሳይንስ የሚናገረው ነገር ከእግዚአብሔር ለመሆኑ ማስረጃ እንደሆነ ሲነገር ብዙ እንሰማለን፡፡ በM.J Fisher, M.DIV የተቀናበረው ‹ተፈጥሮና ሳይንስ በቁርአን› የሚለው ጽሑፍ ሳይንስ ነክ የሆኑትን ጥቅሶች ለቅሞ አቅርቧቸዋል፡፡ በቁርአን ውስጥ ያሉትና ሳይንሳዊ የተባሉት ነገሮች በሳይንስ የሚረጋገጡና ቁርአን የእግዚአብሔር መልእክት መሆኑን የሚያሳዩ ናቸውን? ጽሑፉን እንመልከተው እና እናስብበት፡፡
ግንቦት 8 ፣ 2001 (16 May 2009)
ስለ መሐመድ ምን ያህል ታውቃላችሁ? ብዙ ሙስሊሞች መሐመድን የእስላም ነቢይና ትክክለኛ የአላህ መልክተኛ እንደሆነ፤ ከሌሎችም የጥንት ነቢያት የሚተካከል እንደሆነ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ M. J. Fisher, M.Div በ87 የቁርአን ጥቅሶች ላይ ስለመሐመድ የጻፈውን "መሐመድ በቁርአን" አቅርቦታል:: በማስተዋል ያንቡት፡፡
ግንቦት 1 ፣ 2001 (9 May 2009)
ሙስሊሞች መጽፍ ቅዱስን አምርረው ይቃወማሉ፤ ለምንድነው? የእነሱ መጽሐፍ ስለሚያዛቸው ነውን? አይደለም:: ይህንን የሚያደርጉት በቁርአን ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃወሙ የሚመስሉ ጽሑፎችን በስህተት ስለተረዷቸው ነው፡፡ ይህንን እውነት ለማየት የሚከተለውን "አስመሳይ ጥቅሶች" በሚል ርዕስ የተጻፈውን የM.J Fisher, M.DIV ጽሑፍ ማንበብና ከቁርአን የተጠቀሱትንም ጥቅሶችን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
ቁርአን በበርካታና መልስ በሌላቸው ቅራኔዎች የተሞላ ነው፡፡ የመልስ ለእስላም አዘጋጆች በ<የቁርአን ውስጥ ቅራኔዎች> ከዚህ የሚከተሉትን ለሙስሊም አንባቢዎች አቅርበዋል፡፡ አስተዋይና እውነትን ፈላጊ አንባቢ ወደ ማስተዋል እንዲመጣ ይጋብዛሉ፡፡
ሚያዝያ 16 ፣ 2001 (24 April 2009)
በክርስትና እምነት ውስጥ ትልቅ ስፍራ ከሚሰጠውና የእምነቱ ዋና ማስረጃ ከሚደረገው አንዱ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት ማለትም ትንሳኤ ነው፡፡ የክርስቶስ ትንሳኤ ሎጂካዊ ማስረጃና ማረጋገጫ አለው ወይ? ቁርአን የእግዚአብሔር ቃል ነው በማለት ሙስሊሞች የሚናገሩት ነገር ሎጂካዊ ማረጋገጫና ማስረጃ አለው ወይ? ለሚሉት ጥያቄዎች David Wood የሰጠውን ትንተና በዚህ "የአውራ ጣት ሕግ" በተሰኘ ጽሑፍ ያንብቡ፡፡ አስደናቂ እውነትን ታገኙበታላችሁ፡፡
ርዓን ስለ መሐመድ የሚናገረውና ብዙ ሙስሊሞች የሚያምኑት እሱ ከእግዚአብሔር የተላከ ነቢይ እንደሆነ ነው፡፡ ነገሩ እውነት ነውን? በእርግጥ መሐመድ እውነተኛ ነቢይና የተናገረውም ነገር ሊታመንበት ይገባልን? ይህ የDavid Wood ጽሑፍ የመሐመድ ሳይኮሎጂያዊና መንፈሳዊ አለመረጋጋት ምርመራ ላይ የሚሰጠው ታሪካዊ እውነት በጣም ይረዳዎታል፡፡
ሚያዝያ 12 ፣ 2001 (20 April 2009)
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለክርስትያኖች ተስፋ በተገባው መንግስተ ሰማይና በቁርአን ውስጥ የተገለጠው ፓራዳይዝ ወይንም ገነት መካከል እጅግ በጣም ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ ታዲያ የትኛው ነው እውነተኛ ሁለቱም ትክክል ሊሆኑ ይችላሉን? ይህ የ M. J. Fisher, M.Div. ጽሑፍ (መንግስተ ሰማይ በቁርአን) ይህን እርሰ ጉዳይ በማብራራት ይመረምራል።
በዚህ ጽሑፍ (የቁርአን እርስ በእርስ ተቃርኖ፡ ከማርያም ጋር የተነጋገሩት መላእክት ስንት ናቸው?) Jochen Katz በቁርአን ውስጥ ካሉት የሃሳብ ትቃርኖዎች አንዱን ያሳየናል።
ሚያዝያ 1 ፣ 2001 (9 April 2009)
ቁርአን ስለ ክርስትያኖች ያለውን አመለካከት ያውቃሉን? ክርስትያኖች ትሁታን እንደሆኑ በመንግስተ ሰማይም ልዩ ሽልማት እንደሚጠብቃቸው በመጀመሪያው አካባቢ ይናገርና በስተመጨረሻው ላይ ደግሞ እጅግ ክፉዎች እንደሆኑ ሲዖልም እንደሚገባቸው ይናገራል፡፡ ይህ የM. J. Fisher, M.Div. ጽሑፍ (ክርስትያኖች በቁርአን) እነዚህን ነገሮች ለቅሞ በማውጣት እንድናስተውላቸው ያደርጋል፡፡
የሙስሊሞች ቁርአን ስለ ሲዖል ብዙ ነገሮችን ይናገራል፡፡ ስለዘ ሲዖል ብዙ ነገሮችን አውቆ፣ ከሲዖል የሚዳንበትን መንገድ አንድ ሰው ካላወቀ ስለ ሲዖል ብዙና ዝርዝር ነገሮችን ማወቅ ምንም ጠቀሜታ የለውም። ስለ ሲዖል ማወቅ ከሲዖል ጥፋት በጭራሽ አያድንም፡፡ ይህ የ M. J. Fisher, M.Div. ጽሑፍ (ሲዖል በቁርአን) ስለ ሲዖል ቁርኣን የሚናገረውን ልዩ ልዩ ነገሮች አስፍሯቸዋል፡፡
መጋቢት 28 ፣ 2001 (6 April 2009)
በዓለማችን ላይ እጅግ በጣም ብዙ ሙስሊሞች አሉ፡፡ አንዳንዶች ሙስሊም የሆኑት ከሙስሊም ቤተሰብ በመወለዳቸው እንደሆነ በትክክል ግልፅና የሚታወቅም ነገር ነው፡፡ ግን አንድ ሙስሊም ስለ ሃይማኖቱ ምን ያህል ያውቃል? ስለሃይማኖቱስ ጥያቄዎች የሚሆኑበትን ነገሮች እንዴት ነው የሚያያቸው? እኔስ ሙስሊም ብሆን ኖሮ ምን ማድረግ ነው የሚኖርብኝ? ይህ የ Dallas M. Roak ግሩም ጽሑፍ ሙስሊም ብሆን ኖሮ እያለ አንዳንድ ጥያቄዎችን ያነሳና መልሳቸውን ያሳየናል፤ እናንብበው፡፡
መጋቢት 11 ፣ 2001 (20 March 2009)
መሐመድ ነቢይ እንደሆነና ከእግዚአብሔርም መልእክትን እንደተቀበለ ቁርአንም ሙስሊሞችም ይናገራሉ፡፡ መሐመድ እውነተኛ ነቢይ ለመሆኑ በምን መመርመር ይቻላል? የመጀመሪያው መልስ መሆን ያለበት ቁርዓን የሚሰጠው ውስጣዊ ማስረጃ ነው፡፡ በ Jochen Katz የተጻፈው የመለኮታዊ መገለጥ ድንቁርና?... በቁርዓን ምዕራፍ 3.183 ላይ መሐመድ በተናገረው መገለጥ ላይ ተመሥርቶ የቀረበ ሲሆን መሐመድ እውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ እንዳልሆነ በትክክል የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በማስተዋል እና በጥንቃቄ አንብቡት፡፡
መጋቢት 5 ፣ 2001 (14 March 2009)
የእስልምና እምነት መመሪያ ቁርአን ስለ አላህና ስለ ጌታ ኢየሱስ የሚያስተምረውን ትምህርት መረዳትና ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በ David Wood በተጻፈው "አታላይ አምላክ ብቁ ያልሆነ አዳኝ..." በተሰኘው ጽሑፍ ውስጥ ቁርአን ሙስሊሞች አምላክ ነው የሚሉትን ‹አላህ›ን ታላቅ አታላይ ሲያደርገው፤ ኢየሱስን ደግሞ እንደ-ነቢይም ሆነ እንደ-አዳኝ ብቃት እንዳልነበረው አድርጎ አቅርቦታል።
መጋቢት 2 ፣ 2001 (11 March 2009)
"ለከፍተኛ ዓላማ ተጠራሁ" በ አዛድ ከኢራቅ እና "ሙስሊም በእርግጥ ማወቅ ይችላልን?" በ ዮሴፍ አብርሃም ከግብፅ፤ እነዚህ ሁለት ወንድሞች ወደ ክርስትና እንዴት እንደመጡና በክርስትና ሕይወት ምን እንዳገኙ ይመሰክራሉ።
የካቲት 24 ፣ 2001 (03 March 2009)
ዛሬ ለእስልምና መልስ ፡ አማርኛ ክፍል በኢንተርኔት ይፋ ሲሆን የመጀመሪያ ቀኑ ነው። ወደዚህ ገጽ እንኳን ደህና መጡ! ለጊዘው በግራ በኩል ያለውን ሜኑ በመጠቀም የተለያየ ይዘት ያላቸው፣ አስራ አንድ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ። ወደዚህ ገጽ የሚመጡ ሁሉ የእግዚአብሔርን እውነትና መጠን የሌለው ፍቅር እንዲያገኙ ምኞታችን ነው።
በሳም ሻሞን የተጻፈው "የቁርዓኑ አላህ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ነውን?" በቁርዓኑ አላህ ባህርይና በእግዚአብሔር ባህርያት መካከል ከፍተኛ ልዩነት መኖሩን በትክክል በመግለጽ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር የቁርአኑን አላህ ሊሆን እንደማይችል ያሳያል፡፡ በ "የቁርአን እርስ በእርስ ተቃርኖ፡ ሙስሊሞች ሁሉ ሲኦል ይሄዳሉን?" ሳም ሻሞን ሱረቱ 19.71 ላይ የተመሠረተ ውይይት በማድረግ አዎ ቁርዓን ሲዖል ከመግባት ማንም (ሙስሊም) አያመልጥም እንደሚል ያሳያል። በ "መሐመድ እውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ ነውን?" በሚለው ጽሑፍ ደግሞ ሙስሊሞች መሐመድ የእግዚአብሔር ነቢይ ነው በማለት የሚያምኑት እምነት ትክክል አለመሆኑን የሚያሳዩ ስድስት ሐሳቦችን ያቀርባል፡: በ ሮይ ኦስነቫድ የተጻፈው "መልካምነት በእናንተ ውስጥ ይኖራልን?" መሠረታዊ ክርስትናን ያስተምራል። ሁለት ወንድሞች ወደ ክርስትና እንዴት እንደመጡ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡ "ከሞት የበለጠ ኃይል" በ ሳሚር ከኢራቅ እና "ከእስልምና ወደ ክርስትና የእምነት ጉዞዬ" በ ዩቼል (Yücel) ከቱርክ።
በ "ቁርአን ስለ ፍርድ ቀን" የመጨረሻውን የፍርድ ቀን በተመለከተ እስልምናም ክርስትናም የሚናገሩት በጣም በጥቂቱ ይመሳሰል እንጂ ጉልህ ልዩነቶች እንዳሏቸው እናያለን፡፡ "ለአላህ የተሰጡ ሰዋዊ ባህርያት" ሙስሊሞች ለእግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ተሰጠ የሚሉት አካላዊ ገለጣን በተመለከተ ያላቸው ነቀፌታ መሠረታዊ ችግሮች እንዳሉት ያሳያል፡፡ "ኢየሱስ" የሚለው ዓምድ ሰማንያ ስምንት የቁርዓን ጥቅሶች በመንካት እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ንፅፅር በማድረግ ሙስሊሞች ስለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸው ግንዛቤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በፍፁም የተቃረነ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ከዚህ በላይ ያሉ ሦስት ጽሁፎች ከ "A Topical Study of the Qur'an From a Christian Perspective" by M.J Fisher, M.Div ምዕራፍ 8፣ 13 እና 21 የተተረጎሙ ናቸው።
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ