መሐመድ እውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ ነውን?
Sam Shamoun
[ክፍል አንድ] ክፍል ሁለት
በአዘጋጁ የተቀናበረ
ዋና ሐሳብ ሦስት፡
መሐመድ እጅግ በጣም እርግጠኛ ስህተቶችን አድርጓል፡፡ አንዳንዶቹም ምሳሌዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡-
1. የሌሊት ጉዞ፡
‹ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው ከታምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው) እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡› 17.1፡፡
በእስላሞች ባህል መሠረት መሐመድ ወደ ኢየሩሳሌም መስጊድ ሄዷል፡፡ የሚከተለውም ዘገባ የተወሰደው ከአልፈርድ ጉይላሜስ ስራ ማለትም፡- Alfred Guillaume's The Life of Muhammad (Oxford University Press Karachi, 1995 tenth impression), which is a translation of Ibn Ishaq's Sirat Rasulullah: ላይ ነው፡፡
ዚያድ ቢ. አብዱላህ አል-ባካኢ ከመሐመድ ቢ. ኢሻክ የሚከተለውን ነገረኝ፡፡ ከዚያም ሐዋርያው በሌሊት መካ ካለው መስጊድ ወደ ማስጂድ አላ-አክሳ ማለትም ወደ አሊያ መቅደስ ተወሰደ ይህም እስልምና በኩራይሽና በነገዶች ሁሉ ውስጥ ከተስፋፋ በኋላ ነው፡፡ ያኔም ተጓዳኙ የሆነው ገብርኤል አብሮት ነበር የሄደው፣ በሰማይና በምድር መካከል ያለውን ድንቅ ለማየት ይህም እስከ ኢየሩሳሌም መቅደስ እስከመጣ ድረስ ነበር፡፡
በታሪኩ ውስጥ አል-ሃሰን የሚከተለውን ተናግሯል፡- ‹ሐዋርያውና ገብርኤል ኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ እስከሚደርሱ ድረስ ተጉዘዋል (Guillaume, pp. 181, 182; bold emphasis ours). እንዲሁም ደግሞ ከ Sahih Muslim, Book 1, Number 309: የሚከተለውን እናገኛለን:- በአናስ ቢ. ማክ የተተረከው የአላህ መልእክተኛ (ሰላም በሱ ላይ ይሁን) የተናገረው፤ እኔ ወደ አል-ቡራክ ተወሰድሁ እሱን ነጭና ረጅም የሆነ እንስሳ ከአህያ የበለጠ ነገር ግን ከግመል ያነሰ በሆነ እንስሳ እሱም ሰኮናውን አንድ ምዕራፍ ርዝመት በሚያህል ባለ ቦታ ላይ ያስቀምጣል፡፡ በእሱ ላይ ወጥቼ ወደ ቤተመቅደሱ ወደ ኢየሩሳሌም መጣሁ ከዚያም ነቢያቱ በሚጠቀሙበት ቀለበት ላይ አሰርኩት፡፡ ወደ መቅደሱም ገባሁና ሁለት ራካዎችን ፀለይሁና ወጣሁኝ ከዚያም ገብርኤል የወይን ፅዋና የወተት ፅዋ አመጣልኝ፡፡ እኔም ወተቱን መረጥሁኝ እናም ገብርኤል እንዲህ አለኝ፡- የተፈጥሮ የሆነውን ነገር መርጠሃል፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ ወሰደኝ፡፡
በነዚህ ሁሉ ውስጥ ያለው ችግር የመጀመሪያው የኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ በ587 ዓ.ዓ በባቢሎን ሠራዊት የተደመሰሰ መሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም (የሮሙ) ጄኔራል ቲተስና የእሱ ወታደሮች የኢየሩሳሌምን ሁለተኛውን ቤተመቅደስ በ70 ዓ.ም ፈፅመው ደምስሰውታል፡፡ ስለሆነም ይህ የቤተመቅደሱ መደምሰስ የተከናወነው ይህ የተባለው የኢየሩሳሌም የሌሊት ጉዞ ከመደረጉ በፊት እጅግ በጣም በፊት ነው፡፡ በእርግጥ የተጠቀሰው መስጊድ፣ የመስጂድ አላ-አክሳ የተባለው ቤተመቅደስ እስከ 691 ዓ.ም ድረስ ማለትም አሚር አብዱ-ል-ማሊክ እስከ ገነባው ድረስ በፍፁም ያልነበረ መሆኑ ነው፡፡
(ይህ እንግዲህ የመሐመድን የሌሊት ጉዞ ስህተትነት የሚያረጋግጥ ታሪካዊ እውነታ ነው)
2. የመሬቶች ቁጥር
በቁርዓን መሠረት አላህ የፈጠረው ሰባት ሰማይንና ሰባት ምድሮችን ነው፡፡
‹አላህ ያ ሰባትን ሰማያትን የፈጠረ ነው ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሯል) በመካከላቸው ትእዛዙ ይወርዳል አላህ በነገሩ ሁሉ ቻይ መኾኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በዕውቀት ያካበበ መኾኑን ታውቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)› 65.12፡፡ ጤናማ ሪፖርቶች የሚባለው እንዳረጋገጠው መሐመደ በእርግጥ ሰባት ምድሮች እንደነበሩ ያምን እንደበረ ነው፡፡
በመሐመድ ቢን ኢብራሂም አል-ሃሪት እንደተተረከው፡- ከአቡ ሳላማ ቢን አብዱር-ራህማን በቁራጭ መሬት ምክንያት ከሰዎች ጋር ክርክር የነበረው ሰው ወደ አይሻ በመሄድ ስለጉዳዩ ነገራት፡፡ እሷም ‹ኦ አቡ ሳላማ መሬቱን ተወው ምክንያቱም የአላህ ሐዋርያ፡- ‹ያላግባብ አንድ ስንዝር እንኳን መሬትን የወሰደ ማንም ሰው ቢኖር በአንገቱ ላይ እስከ ሰባት ምድሮች ድረስ ይጠመጠምበታል፡፡› (በማለት እንደተናገረች ነው) (Sahih al-Bukhari, Volume 4, Book 54, Number 417 http://www.usc.edu/dept/MSA/fundamentals/hadithsunnah/bukhari/054.sbt.html#004.054.41; see also Numbers 418, 420; Volume 3, Book 43, Numbers 632
በአቡ ሁራይራህ ደግሞ የተነገረው፡- የአላህ ነቢይ (ሰላም በሱ ላይ ይሁን) እና ጓደኞቹ ተቀምጠው እንዳለ ደመና በእነሱ ላይ መጣ ከዚያም የአላህ ነቢይ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) እንዲህ በማለት ጠየቀ፡ ‹እነዚህ ምን እንደሆኑ ታውቃላችሁን?› እነሱም ሲመልሱ አላህና መልእክተኛው የበለጠውን ያውቃሉ አሉ፣ እሱም አለ፣ ‹እነዚህ ደመናቱ ናቸው፡፡ እነዚህ የምድርን ውሃ ተሸካማዎች ናቸው እነሱም አላህ በማያመሰግኑት እና ስሙን በማይጠሩት ሕዝብ ላይ የሚያመጣቸው ናቸው›፡፡ እሱም ቀጥሎ ጠየቀ፣ ‹ከእናንተ በላይ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?› እነሱም አላህና መልእክተኛው (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) ያውቃሉ ብለው ሲመልሱ እሱም መለሰ፣ ‹እሱ ጠፈር ነው የተጠበቀ ኮርኒስ፣ እና ወደ ኋላ ተመልሶ የተጠበቀ ማዕበል ነው› በማለት መለሰ፡፡ ከዚያም እሱ ጠየቀ ‹በናንተና በእሱ መካከል ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?› እነሱም በመልሳቸው አላህና መልእክተኛው (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) የተሻለ ያውቃሉ አሉ፡፡ እሱም ‹በእናንተና በእሱ መካከል አምስት መቶ ዓመታት አሉ› አለ፡፡ እሱም ከዚያ ጠየቀ፡ ‹ከእርሱ በላይ ያለውን ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?› እነሱም በመልሳቸው አላህና መልእክተኛው (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) ያውቃሉ አሉ፡፡ እሱም ‹በመካከላቸው የአምስት መቶ ዓመታት ርቀት ያላቸው ሁለት ሰማያት አሉ› በማለት መለሰ፡፡ ከዚያም እሱ ሰባት ሰማያትን እስኪቆጥር ድረስ እንደዚያ መናገሩን ቀጠለበት፣ በእያንዳንዱም ጥንድ ውስጥ ያለው ርቀት እንደ ሰማይና ምድር ያለው ርቀት ሆኖ ነው፡፡ ከዚያም እሱ ጠየቀ፣ ‹ከዚያ በላይ ያለውን ታውቃላችሁን?› በማለት እነሱም በመልሳቸው አላህና መልእክተኛው የተሻለ ያውቃሉ በማለት መለሱ፣ እሱም ‹ከዚያ በላይ ያለው ዙፋኑ ነው በዙፋኑና በሰባተኛው ሰማይ መካከል ያለው ርቀትም በእያንዳንዱ ጥንድ ሰማያት ያለውን ርቀት ያህል ነው፡፡› በማለት መለሰ፡፡ ከዚያም ጠየቀ፣ ‹ከእናንተ በታችስ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?› በመልሳቸውም አላህና መልእክተኛው (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) ያውቃሉ አሉ፡፡ እሱም መለሰ ‹መሬት ናት› በማለት፡፡ ከዚያም ጠየቀ ‹ከዚያ በታች ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?› በመልሳቸውም አላህና መልእክተኛው (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) ያውቃሉ አሉ፡፡ እሱም ‹ከእሱ በታች ሌላ መሬት አለ በመካከላቸውም የአምስት መቶ ዓመታት ጉዞ ያህል ርቀት አለ› የሰባት መሬቶችን እና በጥንዶቹም መካከል ያለውን የጉዞ ርቀት እስኪቆጥር ድረስ እንደዚያ በማለት ቀጠለ፡፡ ከዚያም በመቀጠል እንዲህ አለ ‹የመሐመድ ነፍስ በተያዘበችበት በእሱ ወደ ታችኛው መሬት ገመድን ብትጥሉ ከአላህ እውቀት አያመልጥም› ከዚያም የሚከተለውን ቃል አስታወሰ (ቀራ) (ማለትም በመገለጥ ተናገረ) ‹እሱ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነው የውጭውና የውስጡ ነው እሱ ሁሉንም አዋቂ ነው› (ቲርሚድሂ እንደተነተነው የአላህ መልእክተኛ የተናገረው የዚህ ጥቅስ ቃል የሚያመለክተው በአላህ እውቀት፣ ኃይልና ሥልጣን ወዴትም እንደሚወርድ ነው ይህም እሱ በዙፋኑ ላይ እያለ ማለት ነው፣ እሱም በመጽሐፉ ላይ እንደገለፀው ማለት ነው) Ahmad and Tirmidhi transmitted it. (Al-Tirmidhi, Number 1513- taken from the ALIM CD-ROM Version)፡፡
የሙስሊም ተንታኞች በተጨማሪ ማስረጃ የሚያረጋግጡት መሐመድ በስህተት ያምን የነበረው ይህንን እንደነበረ ነው፡፡ እንዲያውም በተጨማሪም የሚናገሩት መሬትም ጠፍጣፋ (ዝርግ) እንደሆነች (ያምን እንደነበረ) ነው፡፡ አንዳንዶቹም ተንታኞች የሚከተሉት ናቸው፡፡
አል-ታባሪ
በመሐመድ ቢ. ሳሀል ቢ. አስካር-ኢስማኢል ቢ. አብድ አል-ካሪም-ዋሂብ፣ አንዳንድ ግርማዊነቱ ተጠቅሰዋል (እነዚህም እንደሚከተለው ተደርገው ተገልፀዋል)፡ ሰማያት እና ምድር እንዲሁም ባህሮች በ ‹ሂካል› ውስጥ ናቸው፣ ሂካል ደግሞ በእግሩ መረገጫ ስር ነው፡፡ የእግዚአብሔር እግሮች ያሉት በእግሩ መረገጫ ላይ ነው፡፡ እሱም የእግሩን መረገጫ ተሸክሟል፡፡ እሱም በእግሩ ላይ ልክ እንደ ሰንደል ጫማ ነው የሆነው፡፡ ዋሂብም ሂካል - ምንድነው? በማለት በጠየቀ ጊዜ፣ እሱም የመለሰው ‹በሰማያት ላይ ያለ አንድ ነገር ነው እሱም ምድርንና ባህሮችን የሚከብብ እና ድንኳን እንደሚታሰርበት ዓይነት ገመድ ነው በማለት መለሰ፡፡› እንደገናም ዋሂብ ምድር ከምን እንደተሰራች በጠየቀ ጊዜ እሱም የመለሰው ‹እነሱም ሰባት ምድሮች ናቸው እነሱም ዝርግና ደሴቶች ናቸው፡ በማለት መለሰ፡፡ በእያንዳንዱ ሁለት መሬት መካከል ባህር አለ፡፡ ሁሉም በሚከባቸው ባህር ተከበዋል እናም ሂካሉ ደግሞ ከባህሩ ጀርባ ነው ያለው፡፡› በማለት መለሰ፡፡ (History of Al-Tabari-General Introduction and From the Creation to the Flood, translated by Franz Rosenthal [State University of New York Press (SUNY), Albany 1989], Volume 1, pp. 207-208;).
ኢብን ካቲር
‹በምድርና በሚመስሉት› ማለት እሱ ሰባት ምድሮችን ፈጥሯል ማለት ነው፡፡ በሁለቱ ሳሂሆች የሚከተለውን የሚገልፅ ሐዲት አለ፡፡
(የአንድን ሰው መሬት ያላግባብ የሚወስድ ማንም ቢሆን ስንዝርም የምታክልን መሬትም እንኳን ቢሆን ከዚያም እሱ በአንገቱ ላይ ተጠምጥሞ እስከ ሰባተኛው መሬት ድረስ ይወርዳል)
በሳሂህ አል-ቡካሪ ቃሉ እንደሚከተለው ነው፡- (እሱ ወደ መሬቶቹ ውስጥ ይሰጥማል)
በመጽሐፌ መጀመሪያ ላይ አል-ቢዳያህ ዋን-ኒሃያህ፣ የዚህን ሐዲት የተለያዩ ትረካዎች ጠቅሻለሁ ይህም የምድርን አፈጣጠር ታሪክ በተረክሁበት ጊዜ ነው፡፡ ምስጋናም ክብርም ሁሉ ለአላህ ነው፡፡
ይህ ሐዲት ሰባቱን ክፍለ ዓለማት ማለቱ ነው በማለት የሚያብራሩት እነዚያ የማያሳምንን ገለጣና የቁርዓንን እና የሐዲትን ቃላት (ፊደላት) የሚፃረርንና እንዲሁም ማስረጃ የሌለውን ነገር አምጥተዋል፡፡ (Tafsir Ibn Kathir (Abridged) Volume 10 (Surat At-Tagabun to the end of the Qur’an), abridged by a group of scholars under the supervision of Shaykh Safiur-Rahman Al-Mubarakpuri [Darussalam Publishers & Distributors, Riyadh, Houston, New York, London, Lahore; first edition, September 2000], pp. 55-56: http://tafsir.com/default.asp?sid=65&tid=54300;)
3. የፀሐይ ምህዋር
ቁርዓንና የመሐመድ ሱናዎች የሚያስተምሩት ፀሐይ ወደምትሰግድበትና እንደገና ለመመለስ ፈቃድ ወደምታገኝበት እስከ አላህ ዙፋን ድረስ እንደምትጓዝ ነው፡፡
‹ፀሐይም ለእርሷ ወደ ኾነው መርጊያ ትሮጣለች፣ ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው› 36.38፡፡
በአቡ ዳር የተነገረው እንደሚከተለው ነው፡- ነቢዩ ፀሐይ በምትጠልቅበት ሰዓት የሚከተለውን ጠየቀኝ ‹ፀሐይ ወዴት እንደምትሄድ ታውቃለህን (በፀሐይ መጥለቂያ ጊዜ)?› እኔም እንደሚከተለው በማለት መለስኩኝ፡ ‹አላህና ሐዋርያው የተሻለ ያውቃሉ›፡፡ እሱም መለሰ ‹ፀሐይ ዙፋኑ ስር ደርሳ እስከምትሰግድ ድረስ እና እንደገናም ለመውጣት ፈቃድ እስከምታገኝ ድረስ ትጓዛለች ነገር ግን (ጊዜ ደግሞ ይመጣል) አጎንብሳ የምትሰግድበት እና ተቀባይነት (ፈቃድ) የማታገኝበት ሰዓት ይመጣል እና ያኔ እንደገና የምታደርገውን እንድታደርግ ፈቃድ የምትጠይቅበት እና የምትከለከልበት ጊዜ ይመጣል ያኔ ወደ መጣችበት እንድትመለስ ትታዘዛለች እናም መውጣቷን በምዕራብም ታደርጋለች፡፡ ይህ ደግሞ የአላህ ዓረፍተ ነገር ትርጉም ነው ‹ፀሐይ የምታደርገውን ጉዞ የምታደርገው በየተወሰነ ጊዜ ነው (ይህም የተደነገገ ነው)፡፡ ይህም የአላህ፣ በኃይል የተከበረው፣ ሁሉን ዐዋቂው (ነገር) ነው› 36.38፡፡ (Sahih al-Bukhari, Volume 4, Book 54, Number421: http://www.usc.edu/dept/MSA/fundamentals/hadithsunnah/bukhari/054.sbt.html#004.054.42)
4. ቁርዓን በተጨማሪ የሚናገረው ነገር የከዋክብት መኖር አንዱ ዓላማ በሰይጣናትና በጂኒዎች ላይ እንዲወረወሩ ነው፡፡
‹ቅርቢቱን ሰማይም በእርግጥ በመብራቶች (በከዋክብት) አጌጥናት ለሰይጣናትም መቀጥቀጫዎች አደረግናት፡፡ ለነርሱም (ለሰይጣኖች) የእሳትን ቅጣት አዘጋጀን› 67.5፡፡ ‹እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አስጌጥናት፡፡ አመጠኛም ከኾነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡ ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል› 37.6-8፡፡ ‹በሰማይም ላይ ቡርጆችን በእርግጥ አድርገናል ለተመልካቾችም (በከዋክብት) አጊጠናታል፡፡ ከተባረረ ሰይጣንም ሁሉ ጠብቀናታል፡፡ ግን (ወሬ) መስማትን የሚሰርቅ ወዲያውኑ አብሪ ችቦ ይከተለዋል፡፡ (ያቃጥለዋል) 15.16-18፡፡ ‹የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም)፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል ጭስም ይላክባችኋል (ሁለታችሁም) አትረዱምም፡፡› 55.33-35፡፡
አንድ አቡ ካታዳ የሚባል ሙስሊም ስለዚህ የሚከተለውን ተናግሯል፡- ‹የእነዚህ ከዋክብት አፈጣጠር ለሦስት ዓላማዎች ነው ማለትም ቀረብ ያለውን ሰማይ ለማስዋብ፣ ሰይጣናትን የሚመቱ ሚሳይሎች ለመሆን፣ እና ተጓዦችን የሚመሩ ምልክቶች ለመሆን ነው፡፡ ስለዚህም ማንም ሰው ከዚህ የተለየ ትርጉምን ለማምጣት ቢሞክር ተሳሳቷል እንዲሁም ደግሞ ጥረቱን ያባክናል እራሱንም ሊያውቀው ከሚችለው የእውቀት ችሎታ በላይ ያስቸግራል› (Dr. Muhammad Taq-i-ud-Din Al-Hillai, Ph.D. [Berlin] & Dr. Muhammad Muhsin Khan, Interpretation of the Meaning of the Noble Quran, pp. 214, 394-395;)
መሐመድ ሰይጣን ቁሳዊ ነገር እንደሆነ የሚያምን ለመሆኑ በጣም ግልጥ ነው ከዚህም በተጨማሪ ሰይጣን በሰው ላይና (በሰው) ውስጥም እንኳን ሽንቱን እንደሚሸናም ያምናል፡፡
በአብዱላ የተነገረው እንደሚከተለው ነው፡- በነቢዩ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) ፊት ስለ አንድ ሰው ተጠቅሶ ነበር እናም ስለእሱ ሲነገር የነበረው ሰውየው እስከ ማለዳ ድረስ ተኝቶ ነበር፣ ለጠዋትም ፀሎት አልተነሳም ነበር፡፡ ነቢዩም ‹ሰይጣን በጆሮዎቹ ላይ ሸንቶበት ነው› አለ፡፡ Sahih al-Bukhari, Volume 2, Book 21, Number 245- see also Volume 4, Book 54, Number 492:http://www.usc.edu/dept/MSA/fundamentals/hadithsunnah/bukhari/054.sbt.html#004.05.492)
‹አብዱላህ (ቢ ማሱድ) የዘገበው ደግሞ እንደሚከተለው ነው፣ ሌሊቱን በሙሉ እስከ ማለዳ ድረስ ስለተኛ ሰው (ለነቢዩ) ተነግሮት ነበር፡፡ እሱም (ቅዱሱ ነቢይ) የሰጠየው አስተያየት፡ ‹ያም ያ ሰው ሰይጣን በጆሮዎቹ ላይ ሽንቱን የሸናበት ሰው ነው› በማለት ነው፡፡ Sahih Muslim, Book 4, Number 1700: http://www.usc.edu/dept/MSA/fundamentals/hadithsunnah/muslim/004.smt.html#004.1700
5. የትኛው ነው ቀድሞ የመጣው ሰማይ ነው ወይንስ ምድር?
ቁርዓን ሰማይ ከመፈጠሩ በፊት ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ በመጀመሪያ እንደተፈጠረ ይናገራል፡፡
‹እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለናንተ የፈጠረ ነው፤ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡› 2.29፡፡ ‹በላቸው፡- እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀኖች ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን? ያ (ይህንን የሠራው) የዓለማት ጌታ ነው፡፡ በርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ በርሷም በረከትን አደረገ በውስጧም ምግቦችን (ካለፉት ሁለት ቀኖች ጋር) በአራት ቀናት ውስጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ ለርሷም ለምድርም ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ አላቸው፡፡ ታዛዦች ኾነን መጣን አሉ፡፡ በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፡፡ በሰማያቱም ሁሉ ነገሯን አዘጋጀ ቅርቢቱንም ሰማይ በመብራቶች አጌጥን (ከሰይጣናት) መጠበቅንም ጠበቅናት ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው (ጌታ) ውሳኔ ነው፡፡› 41.9-12፡፡
ለመሐመድና ለመጀመሪያ ተከታዮቹ የአረብኛው ቃል ቱማ ማለት ተከታታይ ድርጊት (ቅደም ተከተል ድርጊት) ማለት እንደሆነ የልማድ ማስረጃ ይናገራል ይህም ሰማያት የተፈጠሩት ከምድር በኋላ ነው (የሚል ነው)፡፡
‹አቡ ሁራይራ የዘገበው የአላህ መልእክተኛ አጆቼን ይዞ የሚከተለውን አለ፡ የከበረውና ታላቁ አላህ ቅዳሜ ቀን ሸክላን ፈጠረ፣ እሁድ ቀን ደግሞ ተራራዎችን ፈጠረ፣ ከዚያም ሰኞ ዕለት ዛፎችን፣ ማክሰኞ ቀን ደግሞ ድካም (ስራ) የሚጠይቁትን ነገሮች ፈጠረ፣ ከዚያም እሮብ ደግሞ ብርሃንን ፈጠረ፣ ከዚያም ሐሙስ ቀን እንሰሳት እንዲሰራጩ እና አርብ ከአስር በኋላ የመጨረሻውን ፍጥረት አርብ በመጨረሻው ሰዓት ማለትም በከሰዓት በኋላና በምሽት መካከል አዳምንም (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) ደግሞ ፈጠረ›፡፡ (Sahih Muslim, Book 039, Number 6707: http://www.usc.edu/dept/MSA/fundamentals/hadithsunnah/muslim/039.smt.html#039.6707
ይህ የሐዲት ዘገባ የሚያስረዳው የብርሃንን መፈጠር እሮብ እንደሆነ አድርጎ ነው ይህም ከምድርና በውስጧ ካለው ነገር ሁሉ በኋላ (የተፈጠረች) መሆኑ ነው፡፡ ብርሃን የሚያሳየውም ፀሐይን ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ከዘመናዊው የሳይንስ ፅንስ ሐሳብ ጋር ሙሉ ለሙሉ የሚቃረን ነው፣ ምክንያቱም ሳይንስ በዩኒቨርስ አመጣጥ ላይ ከማንኛውም እፀዋት በፊት የፀሐይን መኖር ያስቀምጣልና፡፡
የሚከተለውም ልማዳዊ ዘገባ ከ The History of al-Tabari, Volume 1 - General Introduction and from the Creation to the Flood (translated by Franz Rosenthal, State University of New York Press (SUNY), Albany 1989), pp. 187-193. ላይ ተወስዷል እሱም እንደሚከተለው ይላል፡-
‹እኛ የገለፅነው ከዚያ ጊዜ በፊት ያለው የሌሊትና የቀን ሰዓታት ናቸው ይሁን እንጂ ሰዓታቶቹ በፀሐይና በጨረቃ ክበብ ዲግሪ መሠረት ተለዋዋጭ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን ይህ በእንደዚህ እንዳለ በአላህ መልእክተኛ የተነገረን ትክክለኛ የሆነ የልማድ ገለፃ አለን ይህም በሃናደ ቢ. አል-ሳሪ ነው፣ እሱም ያለው ሐዲቶችን ሁሉ አንብቦ (ለአቡ-በከር) አቡ በከር ቢ. አያሽ - አቡ ሳኣድ አል - ባካል - ኢክሪማህ - ኢብን አባስ፡ አይሁዶች ወደ ነቢዩ መጥተው ስለ ሰማይና ምድር አፈጣጠር ጥያቄን ጠየቁት፡፡ እሱም - እግዚአብሔር ምድርን እሁድና ሰኞ ፈጠረ፡፡ ማክሰኞ ደግሞ ተራራዎችንና የያዙትን ጥቅም ፈጠረ፡፡ እሮብ ዕለት ደግሞ ዛፎችን ውሃን ከተሞችንና የሚታረሰውን ባዶውን ምድር ፈጠረ፡፡ እነዚህ አራት ቀናት ናቸው፡፡ እሱም ቁርዓንን በመጥቀስ ቀጠለ ‹በእርግጥ እናንተ ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው እና ሌሎችንም እንደሱ ያሉትን ባስቀመጠው አታምኑምን? እሱም የዓለማት ጌታ ነው፡፡ እሱም በጣም ጥብቅ እንዲሆን አድርጎ ሰራው (ተራራዎችን) በላያቸው ላይ አድርጎ ከዚያም ባረከው እና የሚሰጠውን የምግብ መጠን እንዲይዝ አደረገው፣ ይህም የሆነው ሁሉ በአራት ቀናት ውስጥ ነው እኩል ለሚጠይቁት ሁሉ› - ለእነሱ - ሐሙስ ቀን ሰማይን ፈጠረ፡፡ አርብ ደግሞ ከዋክብትን ፀሐይን፣ ጨረቃን እና መላእክትን ፈጠረ ይህም ሦስት ሰዓት እስከሚቀር ድረስ ነው፡፡ በነዚህ ሦስት ሰዓታት መጀመሪያ የሰውን ሕይወት ሁኔታዎች ፈጠረ፣ እኛ እንድንኖርና እንድንሞት፡፡ በሁለተኛው ሰዓት ውስጥ ደግሞ ለሰው ልጅ ጠቃሚ በሆነው ነገር ሁሉ ላይ ችግርን (ጉዳትን) ጣለበት፡፡ በሦስተኛው ሰዓት ደግሞ አዳምን ፈጠረና በፓራዳይዝ እንዲኖር አደረገው፡፡ ከዚያም ኢብሊስን (ሰይጣንን) በአዳም ፊት እንዲሰግድ አዘዘው ከዚያም በሰዓቱ መጨረሻ ላይ አዳምን ከፓራዳይዝ ውስጥ አስወጣው፡፡ አይሁዶችም፣ ‹ከዚያስ - ምን መሐመድ?› ብለው በጠየቁት ጊዜ እሱም፡ ‹ከዚያም እሱ በዙፋኑ ላይ ቀጥ ብሎ ተቀመጠ› አላቸው፡፡ ከዚያም አይሁዶቹ፣ ጨርሰህ ከሆነ ትክክል ነህ አሉና፣ ቀጥለውም እነሱ ‹ከዚያም አረፈ› ከሚል ጋር ብለው አሉ፡፡ በዚህም ነቢዩ በጣም ተናደደ እና የሚከተለው መገለጥ ተገለጠለት፡ ‹እኛ ሰማይንና ምድርን እንዲሁም በመካከላቸው ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ ፈጠርን ድካም ግን አልነካንም› አለና፤ ‹ስለዚህም ለምትናገሩት ነገር ሁሉ ትዕግስት ይኑራችሁ› አለ፡፡
እናም
‹በአል-ሙታና - አል ሃጃጅ - ሐማድ - አታ ቢ. አል-ሳኢብ አክሪማ አባባል፡ አይሁዶች ነቢዩን ጠየቁት፡ እሁድስ? በማለት የእግዚአብሔርም መልእክተኛ መለሰ፡ በእሱም እግዚአብሔር ምድርን ፈጠረና አስፋፋት አለ፡፡ ስለ ሰኞም ጠየቁት እሱም ሲመለስ፡ በእሱም አዳምን ፈጠረ አላቸው፡፡ ስለ ማክሰኞም ጠየቁት እሱም መልሶ፡ በእሱም ተራራዎችን ውሃን እና ወዘ.ተ. ፈጠረ አላቸው፡፡ ስለ እሮብም ጠየቁት እሱም መልሶ፡ ምግብ አለ፡፡ ስለ ሐሙስም ጠየቁት፡ እሱም መልሶ ሰማያትን ፈጠረ አላቸው፡፡ እነሱም ስለ አርብ ጠየቁት እሱም መልሶ፡ እግዚአብሔር ቀንንና ሌሊትን ፈጠረ አላቸው፡፡ ስለ ቅዳሜም ጠየቁትና እግዚአብሔር በእሱ አረፈ አሉት፣ እሱም ጮክ ብሎ እግዚአብሔር ይመስገን! አለ ከዚያም እግዚአብሔር ‹እኛ ሰማይንና ምድርን እና በመካከላቸውም ያለውን በስድስት ቀናት ውስጥ ፈጠርን እና ምንም ድካም አላየንም› የሚለው መገለጥ መጣለት፡፡
ነገር ግን የሚከተለው የቁርዓን ቁጥር ከዚህ በላይ ያለውን ዓረፍተ ነገር በመቃረን በምድር ላይ ያሉት ነገሮች እንደ ውሃ ያሉት ሰማያት ከተፈጠሩ በኋላ እንደተፈጠሩ ያረጋግጣል፡
‹ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? (አላህ) ገነባት፡፡ ከፍታዋን አጓነ አስተካከላትም፡፡ ሌሊቷንም አጨለመ ቀንዋን ገለጸ፡፡ ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡ ውሃንና ግጦሿን ከርሱ አወጣ፡፡ ጋራዎችንም አደላደላቸው፡፡ ለናንተና ለእንስሶቻችሁ መጠቀሚያም ይኾን ዘንድ (ይህን አደረገ)› 79.27-33፡፡
አል-ታባሪ ‹ባኣ-ዳ› ስለሚለው ቃል የሚከተለውን ጽፏል፡ አንድ ሰው እንዲህ ሊል ይችላል፡ እናንተ እንደምታስተውሉት ብዙ ተንታኞች የእግዚአብሔርን ቃል አስተውለውታል፡፡ ‹ከዚያ በኋላ የዘረጋው ምድርን ነው› ማለትም ‹በአንድ ጊዜ ነው የዘረጋት› ‹ይህም ‹ባኣ-ዳ›፣ ‹በኋላ› ለሚለው መስተዓምር ማለትም ‹ማ-ኣ› ‹አንድ ላይ (በአንድ ጊዜ)› የሚል ነው በማለት ነው፡፡ አሁን ለዓረፍተ ነገራችሁ ትክክለኛነት ማለትም እዚህ ጋ ላለን ‹በኋላ› ለሚለው ትርጉም ያም ‹በፊት› ከሚለው ተቃራኒ ቃል ይልቅ ያላችሁ ማስረጃ ምንድነው? ለዚህም የሚሆነው መልስ በአረብኛ አነጋገር ውስጥ ‹በኋላ› የሚለው ቃል ትርጉም ከዚህም በፊት እንደተናገርነው የ ‹አስቀድሞ› ወይንም ‹የ በፊት› የሚለው ቃል ተቃራኒ ነው እንጂ ‹በአንድ ላይ› ወይንም በአንድ ወቅት የሚል ትርጉም አይደለም፡፡ እንግዲህ አሁን የቃላት ትርጉሞች ተግባራዊነትን ስንመለከት ከሁሉ በላይ ቋንቋውን በሚያውቁት ተናጋሪዎች ዘንድ ነው የሚታወቀው እንጂ በሌሎች አይደለም፡፡ (Ibid., p. 216;)
የቅርቡ የሙስሊም ተርጓሚ አብዱላህ ዩሱፍ አሊ በቁርዓን 79.30 ላይ ያለውን ‹ከዚህ በኋላ› የሚለውን ቃል ማለትም ‹ባኣ"ዳ› ሲተረጉም፤ የተረጎመው ‹ከዚህም በላይ› ብሎ ሲሆን በትህትና የተቀበለው ‹ከዚህም በላይ› ወይንም በጣም ጥሬ በሆነ መልኩ ‹ከዚያም በኋላ› ማለት ነው ብሎ ነው፡፡ See n. 4475 to xli. 11. (Ali, footnote 5937)፡፡
የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-
ከዚህ በላይ ባየናቸው ቁርዓናዊ ግልፅ የሆኑ አምስት አባባሎች መሠረት አንድ እውነት ሊገባን ያስፈልጋል፡፡ ይህም ቃላቶቹን የተናገረው እውነተኛ ነቢይ ሊባል እና በሕይወታችን ውስጥ ዋና በሆነው የዘላለም ሕይወት ጉዳይ ላይ ልንከተለው ይገባል ወይ? የሚለው ነው፡፡
በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ የሚከተለው ሃይማኖት ወሳኝነት አለው፡፡ አንድ ሰው የሚከተለው ሃይማኖት ትክክል መሆን አለመሆኑን መመርመርና እውነትን መፈለግ ይገባዋል፡፡ የነቢዩ መሐመድ ከአላህ የመጡ ናቸው የተባሉት አምስቱ ነጥቦች ሙሉ ለሙሉ ስህተቶች ናቸው፡፡ ታዲያ ምን ማድረግ ይገባናል? ስህተተን በመከተል መኖርና የስህተትን እምነት ፍርድ መቀበል? ወይንስ አሁን ስህተት ሲገለጥልን በማስተዋል ወደ እውት መምጣት? ምርጫውን ለአንባቢ እንተወዋለን፡፡ የራሳችን አስተያየት ግን አንባቢ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው እውነት የሆነውን የጌታ ኢየሱስን ወንጌል እንዲያነብ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል አንብቡ፡፡ በቃሉም መሠረት እራሳችሁን መርምሩ የዘላለምንም ሕይወት ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር ምህረት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል - ኑ - አትዘግዩ እግዚአብሔርም ይርዳችሁ አሜን፡፡
የትርጉም ምንጭ: Is Muhammad a true Prophet of God?
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ