ቁርአን ከእግዚአብሔር የመጣ ሊሆን አይችልም
በ Bassam Khoury
ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ
ቁርአን ያቀረበው ‹የአላህ ፅንሰ ሐሳብ› ቁርአን እራሱ ከእግዚአብሔር መገለጥ የመጣ መሆኑን የማይቻል ያደርገዋል፡፡ ይህንን ለመረዳት አንድ የቁርአንን ጥቅስ በጣም ጠጋ በማለት እንመልከት፡
‹.... .... በርሱ ያበዛላችኋል፣ የሚመስለው ምንም ነገር የለም፤ እርሱም ሰሚው፡ ተመልካቹ ነው፡፡› 42.11፡፡
ለመጀመርም፣ ቁርአን እንደሚያቀርበውና ሙስሊሞችም በዚህ መሠረት እንደሚናገሩት የአላህን ባህርያት የምንመረምር ከሆነ፣ የምናገኘው ነገር እነዚህ ነገሮች በቁርአን 42.11 ላይ ያሉት ትርጉመ ቢስ ቃላት ሆነው ነው፡፡ የNahj Al-Balagha ጸሐፊ የአላህን ባህርይ ሲተረጉም የተናገረው እንደሚከተለው ነው፡-
‹በሃይማኖት ውስጥ የመጀመሪያው ነገር እርሱን ማወቅ ነው፣ እርሱንም ማወቅ ፍፁምነት ያለው እሱን በማወጅ ላይ ነው፣ የእሱንም ማወጅ ፍፁምነት ያለው በእርሱ አንድነት በማመን ላይ ነው፣ በእርሱም አንድነት የማመን ፍፁምነት ያለው እርሱን ንፁህ አድርጎ በመቁጠር ላይ ነው፣ የእርሱ ንፁህነት ፍፁምነትም ያለው እርሱ ባህርያት የሉትም በማለት ላይ ነው፣ ምክንያቱም እያንዳንዱ ባህርይ፤ - ባህርይ ተብሎ ከተነገረለት ከእያንዳንዱ ነገር የተለየ መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም ለአላህ ባህርይን የሚያያይዝ (ወይንም የሚሰጥ) ማንም ቢኖር እርሱ የሚያደርገው ነገር የእርሱን ምስያ መስጠቱ ነው፣ የእሱንም ምስያ የሚሰጥ ማንም ቢኖር ደግሞ የሚያደርገው ነገር እርሱ ሁለት ነው ማለቱ ነው፣ ማንም እርሱ (አላህ) ሁለት ነው የሚል ከሆነ ደግሞ እርሱ ሸሪክ (አካል) አለው ማለቱ ነው፣ ማንም ለእርሱ ሸሪክ (አካል) አለው የሚል ደግሞ እርሱን ይስተዋል (በተሳሳተ መንገድ ያየዋል) እርሱን የሚስተው ደግሞ ወደ እርሱ ይጠቁማል፣ ወደ እርሱ የሚጠቁም ማንም ቢኖር ደግሞ እርሱ ውሱንነት አለው ማለቱ ነው፣ ማንም ለእርሱ ውሱንነትን የሚሰጥ ቢኖር ደግሞ እርሱን (ውሱን አድርጎ) ይቆጥረዋል ማለት ነው፡፡ ማንም እርሱ ማለት እንዲህ ነው የሚል ቢኖር፣ የሚለው እርሱ በአንድ ነገር የተያዘ ነው ማለቱ ነው፣ ማንም እርሱ እንዲህ ነው ቢል እርሱ በአንድ ነገር አለ ቢል፣ እርሱ በምንም ነገር ውስጥ የለም፡፡ እርሱ ሕልውና ያለው ነው፣ ነገር ግን የኖረው በሆነ ክስተት ውስጥ በመግባት አይደለም፡፡ እርሱ ይኖራል ነገር ግን ከማይኖሩ አይደለም፡፡ እርሱ ከሁሉም ነገር ጋር ነው ነገር ግን በአካላዊ (በቁሳዊ) ቅርርብ አይደለም፡፡ እርሱም ከቁሳዊ ነገር ሁሉ የተለየ ነው ነገር ግን በአካላዊ ልዩነት አይደለም፡፡ እርሱ ያደርጋል ነገር ግን ከእንቅስቃሴ አባባል ወይንም የመሳሪያ ዓይነት ስሜት ባለው መልኩ አይደለም፡፡ በፍጥረት መካከል ምንም የሚታይ ነገርም እንኳን ሳይኖር እርሱ ያያል፡፡ እርሱ ብቸኛ አንድ ነው፡፡ ስለዚህም እርሱ ከሌሎች ጋር ህብረትን አያደርግም ካለማድረጉም የተነሳ እርሱ እጦት የሚሰማው አይደለም፡፡›
Ibn Ishaq Al Kindy1 says: እንደተናገረው ‹አላህ የተባረከና የተከበረ ይሁንና ፍፁም አንድ ነው፣ እንዲሁም ደግሞ ምንም ብዙነትንና ድብልቅን አይፈቅድም፡፡ እርሱ ከመገለጥ በላይ ነው፣ እንዲሁም በምንም ዓይነት ሁኔታ ሊገለጥ አይቻልም› (The magazine of the University of Umm-Al-Qura, Vol. 6, p. 123) ፡፡
ይህ ነው እንግዲህ አላህን በተመለከተ የሚኖረውን ማንኛውንም ንግግር ትርጉመ ቢስ የሚያደርገው፡፡ ይህም የግል ማገናዘቢያን መምታትን እንደሚሰጥ የሚለውን ላለመጥቀስ ነው፡- አላህ በምንም ነገር ሊገለጥ የማይቻል ነው፣ ድብልቅ ሊሆን በማይችል ነገር ውስጥ ነው ያለው፡፡ ወይንም አላህ ያለው በራሱ ተፈጥሮ ውስጥ ነው ማለትም በሌላ ምንም ነገር ጋር ሊደመር በማይችል ነገር ውስጥ ነው፡፡ ወይንም አላህ መገለጥ ያለበት ሊገለጥ የማይችል ነገር ሆኖ ነው፡፡
ሙስሊሞች እንደዚህ ዓይነት አመለካከት ያላቸው ሰዎች የሱና ሰዎች አይደሉም በማለት ሊናገሩ ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሱሂ ሙስሊሞች ከዚህ በላይ ከተጠቀሰው አመለካከት ላይ ምንም የሚለዩበት መሻሻልን አላደረጉም፡፡ የሱኒ ሙስሎሞች የአላህን ስምና ባህርያትን በተመለከተ የሚያስተምሩት ትምህርት እንደሚከተለው ነው፡- ‹የአላህ ስም እርሱ ይክበርና - በቁርአን እና በሱና መሠረት፣ ያለምንም ጭማሪ ወይንም ቅነሳ፣ እንዲሁም የአላህን ስም እጅግ ታላቅነት፣ ምክንያት (የሰው ግንዛቤ) ሊገነዘባቸው ስለማይችል በጥቅሱ ላይ ብቻ መወሰን በፍፁም አይቀሬ ነው› የሚል ነው፡፡ (Al-Majla Sharh Al-Akeeda Al-Muthla – Ibn Otheimeen 1:8)፡፡
በዚህ ነጥብ ላይ የሱኒ ሙስሊሞች የሚግሩን ነገር በመጽሐፉና በአላህ መሠረት ለአላህ የሚገባውን ነገር እንደሚያረጋግጡልን ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ምንም ነገርን አይገልጥልንም፣ እኛ የተቀበልነው ነገር እነዚያ ባህርያት እዚያ ውስጥ እንዳሉ ነው፡፡ ችግሩ አሁን እነዚህን በሙስሊሞች ትምህርት መሰረት ስንመለከታቸው እነሱ በሙሉ ባዶ ቃላት ብቻ መሆናቸውን እናገኛለን፡፡ የቁርአን 42.11 ክፍል የሚነግረን ‹እርሱ ሁሉን የሚያይ ሁሉን የሚሰማ› እንደሆነ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ቃላት በሱኒ ሙስሎሞች መሠረት ምን ማለት ናቸው? እዚህ ላይ የሱኒዎችን እምነት ማየት ያስፈለገበት ምክንያት ሌሎቹ ከዚህ ውይይት ውስጥ እራሳቸውን ስላገለሉ ነው፡፡ ይህም በራሳቸው ፈቃደኝነት ነው እንደ ሺያዎች ለምሳሌ እንዳስቀመጡት፡- ‹የእርሱ ንፁህነት - ፍፁምነት የእርሱን ባህርያት መካድ ነው› በእርግጥ ደግሞ ‹እርሱ በምንም ነገር ሊገለጥ አይቻልም›፡፡
ለሱኒዎች ግን ባህርያቱን ያረጋግጣሉ ነገር ግን የሚናገሩት የሱኒዎች መሰረታዊ እምነት አላህ መገለጥ ያለበት እርሱ እራሱን በገለጠበት ገለጣ ነው፡፡ ወይንም ደግሞ የአላህ መልእክተኛ (በረከት በእርሱ ላይ ይሁንና) እርሱን ያለምንም ማወዳደሪያ ወይንም ምስያ ወይንም ትርጉም እና በሽረት አባባል (አይደለም በማለት) በገለጠበት ነው፡፡
የአላህ ባህርያት ማረጋገጫ እና ሌሎች ባህርያት እነሱን ከሰዋዊ ባህርያት ጋር የማገናኘት አስፈላጊነትን ጥረት አይጠይቅም፡፡ በእርግጥም እነሱ ከሰዎች ባህርያት ጋር ተመሳሳይ አይደሉም ነገር ግን ከእርሱ ታላቅነት (ግርማዊነት) እና ክብር ጋር የሚስማሙ ናቸው፡ እርሱን የሚመስል ነገር የለም፣ ‹እርሱ ሁሉን የሚሰማው ነው እርሱ ሁሉን የሚያይ ነው›፡፡ 42.11፡፡
አንዳንድ ነገሮችን ለመረዳት እንድንችል እዚህ በጥቅም ላይ የዋሉትን ቃላት መረዳት ይኖብናል፡፡
መምሰል፡- የአላህ ማንኛውም ባህርያት እንደ ሰው ባህርያት አለመሆናቸውን ማመን ነው፡፡
ማመሳል፡- የአላህ ባህርያት ከሰው በህርያት ጋር ተመሳሳይነት እንዳላቸው ማመን ነው፡፡
የሉም ማለት፡- የአላህን ባህርያት ወይንም አስተዋፅዖዎችን ሙሉ ለሙሉ የሉም በማለት መካድ፡፡
መተርጎም፡- ቃላቶቹን ግልፅ ከሆነው ትርጉም በተለየ በሌላ መንገድ ለመረዳት መሞከር ማለት ነው፣ ለምሳሌም ‹እጅ› ማለት ኃይል ነው፡፡ ወይንም ‹ዓይን› ማለት ደግሞ ጥበቃ ነው፣ ወይንም ያንን የመሰለ ማንኛውም ነገር፡፡
በትርጉሞቹ ስር ማንኛውንም ቃል ለመረዳት በጭራሽ አይቻልም፡፡ ‹ሁሉን የሚሰማ፣ ሁሉን የሚያይ› 42.11 የሚሉትን ትርጉም እንጠይቅ ብንል፣ መልሳቸው የሚሆነው፣ ‹ሁሉን የሚሰማ እና ሁሉን የሚያይ ነው›፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ትርጉም በሙስሊሞች መሠረት በሰዋዊ ሐሳብ ውስጥ በሚቀረፅ በማንኛውም ስዕል ወይንም እይታ ጋር በምንም መልኩ መያያዝ አይኖርበትም፡፡ የእነሱም ሊቃውንት ይህንን አጥብቀው የሚናገሩት፡- ‹አላህ ክብርና ኃይል ለእሱ ይሁን በሰዎች የታሰበ ወይንም የተገመተ ባህርይ በራሱ አለው በማለት መናገር በፍፁም አይቻልም በማለት ነው ምክንያቱም አላህ ከማንኛውም ከምታስቡት ነገር ሁሉ በጣም የተለየ ነው› (The Explanation of the Tahawi’s belief – Saleh Al Al-Sheikh – a lecture on Saturday 13 Thee Al Kaadeh, 1417 H - quoted from the Comprehensive Encyclopaedia; source, page (1/168)) ፡፡
ነገር ግን እንደዚህ ዓይነት ቃላት የማይተረጎሙ ከሆነ፣ ስለዚህም አላህ ‹ሁሉን የሚያይ› በሚለውና ‹ሁሉን የሚሰማ› በሚለው መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? በእንደዚህ ዓይነት አቀራረብ እንደዚህ ዓይነቶቹ ሁሉ የአላህ ባህርያት ተንኮታኩተው የሚወድቁት በአንድ ትርጉም የሌለው ባህርይ ውስጥ ነው፡፡
የአላህ ባህርያት ከፍጥረት ባህርያት ጋር እንኳን የሚስማማ ነው ብንልም በሙስሊሞች መሰረት እነዚህ የሚሉት አንድ ዓይነት ነገርን አይደለም፡፡ ስለዚህም ሙስሊሞች የሚከተለውን ይላሉ፡ ‹ለአንድ ሰው፣ አላህ ያውቃል እኔም እውቃለሁኝ፣ አላህ ይኖራል እኔም እኖራለሁኝ፣ አላህ የሚኖር ነው እኔም እኖራለሁኝ፣ አላህ ይችላል እኔም እችላለሁኝ በማለት ማንም ሊናገር አይፈቀድለትም፡፡ ይህንን ነፃ በሆነ መንገድ እኔ መናገር የለብኝም ነገር ግን የአላህን እውቀት ችሎታ ሕልውና እና ሕይወት ከእኛ እውቀት፣ ከእኛ ችሎታ፣ ከእኛ መኖርና ሕይወት በተለየ መልኩ ነው፡፡› (The Essence of Explaining the Islamic belief - the subject of Allah’s characteristics; source, 3rd point: The un-likeness to creation)፡፡
ከዚህ በላይ የቀረበውን ወይይት በሎጂካዊ መንገድ ብንመለከተው የምናገኘው ነገር ቢኖር የእስልምና ትምህርት፣ የቁርአንን ከእግዚአብሔር በመገለጥ የመጣ ነው የሚለውን ነገር በፍፁም የማይቻል ያደርገዋል፡፡ ምክንያቱም፡-
1. ቁርአን ስለ አላህ የሚናገረው፣ እርሱን የሚመስል ምንም ነገር እንደሌለ ነው፡፡
2. ይህም ማለት - ‹አላህ› - በምትሉበት ጊዜ ስለ እርሱ ወደ አዕምሯችሁ ከሚመጣው ማንኛውም ነገር ሁሉ እርሱ የተለየ ነው፡፡
3. ሙስሊሞች በ‹ሙካላፍት›፣ ‹የማይመስል› ዶክትሪን ወይንም አስተምህሮ ያምናሉ፣ ማለትም በአላህና በባህርያቱ መካከል በምንም መልኩ ቢሆን ምንም መመሳሰል የለም ይላሉ፡፡ ይህም በአንድ በኩል ከራሱ ባህርያት ጋር እና በሌላው ጎኑ ደግሞ ከፍጥረታቱ ባህርያት ጋር፡፡
4. ቁርአን የአላህ ቃል ነው እንደ ሰው ቃል ያልሆነ ነው፡፡
ከዚህ በላይ ያሉት እንደሚያሳዩት ከሆነ ስለ አላህ ለመነጋገር የሰውን ቋንቋ መጠቀም አይቻልም፡፡ ይህ ደግሞ ቁርአን ስለ አላህ ተፈጥሮ እና ባህርያት የሚናገረው እውነት ከሆነ ወይንም ታማኝነት ያለው ከሆነ፣ ቁርአን እራሱ ከአላህ የመጣ መገለጥ አይደለም ማለት ነው፡፡ በሌላ አባባል ውሸት ከሆነ ውሸት ነው ማለት ነው፡፡ እውነት ከሆነ ደግሞ እውነት ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህም እርሱ ውሸት ነው፡፡
የዚህ የቁርአን ትምህርት ዋና ነጥብ ‹አላህን በሰው ቋንቋ መግለጥ አይቻልም› የሚል ነው፡፡
ስለዚህም ቁርአን በሰዎች ቋንቋ የተጻፈ በመሆኑ የአላህ መግለጫ ሊሆን አይችልም ማለት ነው፡፡ ከእርሱም የመጣ መገለጥ ሊሆን አይችልም፡፡ እንዲሁም የእሱ ቃልም ሊሆን አይችልም፡፡
ማለትም ቁርአን አላህ ማንነው በሚባለው ነገር ላይ እውነተኛ ከሆነ፣ ቁርአን ምን በመሆኑ ላይ ግን እውነተኛ ሊሆን አይችልም፡፡ የዚህ ግልባጭ ገለጣም ትክክል ነው ማለት ነው፡፡
ለሙስሊሞች ይህንን መምታታት ለማስወገድ (ለመፍታት) ያለው ብቸኛ መንገድ በቁርአን ውስጥ ያሉት ቃላቶች በሙሉ ከእውነታ ውጪ የሆኑ መሆናቸውን በመገንዘብ እና ከማንኛውም የሰው ልጅ ፅንሰ ሀሳብ ጋር አብረው ሊሄዱ የማይችሉ መሆናቸውን ነው፡፡ ይህም ቃላቶቻቸው ሁለቱም እንኳን ሊስማሙ ቢችሉም እንኳን ነው፡፡ በሌላ መንገድም ሲገለጥ እነዚያ ቃላት ምንም ትርጉም የላቸውም ማለትም አውነታው እነሱ ባዶ ቃላት ብቻ መሆናቸው ነው፡፡
ስለዚህም በሙስሊሞች ትምህርት መሠረት ስለ አላህ ሎጂካል በሆነ መንገድ በአዕምሮችን የሚመጣው ነገር ከአላህ የተለየ ነው፡፡ በመሆኑም ቁርአን ስለ አላህ የሚለውን ደግሞ ከተረዳን፣ ቁርአን ስለ እርሱ ከሚናገረው ነገር ሁሉ የተለየ ነው ማለት ነው፡፡
የአዘጋጁ ማሳሰቢያ
ከዚህ በላይ እንደተመለከትነው የአላህን ወይንም ሙስሊሞች አምላክ የሚሉትን ማንነት በትክክል ማስቀመጥ ለእስልምና ሃይማኖት እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ከጽሑፍ ሎጂካዊ አቀራረብ እንዳየነው፡ ቁርአን ስለ አላህ የሚናገረውን እውነት ነው በማለት ከተቀበልን በቀጥታ የምንመጣው ቁርአን የሚባለው መጽሐፍ ከአላህ የመጣ ሊሆን አይችልም ወደሚል ትክክለኛ መደምደሚያ ነው፡፡ በአጭሩ ቁርአን የአምላክ መጽሐፍ ሊሆን አይችልም ማለት ነው፡፡
ይህ ሎጂካዊ እውነት ብዙ ጥያቄዎችን በአዕምሮአችን ሊያስነሳ ይገባዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፣ የማመልከውን አምላክ ላውቀው እችላለሁ ወይ፣ እርሱስ ምን ዓይነት ባህርይ አለው? ለሚያምኑትስ ምን የሚሰጠው ጠቀሜታ አለው፣ ለአማኞቹስ የሚሰጠውን ጠቀሜታ መናገር ይቻላል ወይ? እንደ አንድ አማኝስ የእኔ ተስፋ ምንድነው? ወ.ዘ.ተ ሊጠየቁ ይገባል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የሚያቀርበው እግዚአብሔር ግን ሊታወቅ የሚችል ነው፡፡ እርሱ እራሱን በፍጥረት እንዲሁም በቃሉ ውስጥ ገልጧል፡፡ ሰዎች ያለምንም ውዥንብር እንዲያውቁት፣ እንዲያምኑትና እንዲታመኑበት ይጋብዛል፡፡ ትልቁን እና ልዩ የሆነውን የእራሱን መገለጥ የገለጠው በክርስቶስ ኢየሱስ ስጋ ለብሶ መምጣት ውስጥ ነው፡፡
የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ እግዚአብሔር ሰዎችን ከኃጢአታቸው ለማዳን በመፍቀዱና በመውደዱ ያዘጋጀው የደኅንነት መንገድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ስጋ ለብሶ ሰው እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ሰው የሆነውም አምላክ ማለትም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰዎች ኃጢአት ቅጣት ምትክ ሆኖ ተቀጣ፡፡ የእግዚአብሔርንም ፍቅር እና ፀጋ በተግባር ለሰዎች አሳየ ገለጠም፡፡ እንግዲህ በእርሱ በማመን ኃጢአታቸውን በእግዚአብሔር ፊት በመናዘዝ እርሱ በሰራው ስራ በኩል እግዚአብሔር እንዲቀበላቸው የሚጠይቁ ሁሉ ከእርሱ ምህረትን እና የዘላለም ይቅርታን ይቀበላሉ፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር አባታቸው እነርሱ ደግሞ የእርሱ ልጆች በመሆን በእውነተኛ መንፈሳዊ ህብረት ከእግዚአብሔር ጋር ይኖራሉ፡፡
የዚህ ገፅ አዘጋጆች ዋና ፍላጎት ሰዎች ይህን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር የገለጠውን ምህረት እንዲያገኙና ዘላለምን ከእርሱ ጋር እንዲያሳልፉ ነው፡፡ አንባቢዎች ሆይ የእግዚአብሔርን ምህረት ተቀብላችኋልን? ለመቀበላችሁስ ማረጋገጫ አላችሁን? ይህንን ማወቅና ማረጋገጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፣ ለምን ትዘገያላችሁ? ወደ እግዚአብሔር ምህረት በክርስቶስ በኩል ዛሬውኑ ኑ ጌታም በምህረቱ ይርዳችሁ አሜን፡፡
የትርጉም ምንጭ: The impossibility of the revelation of the Qur'an
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ