ለከፍተኛ ዓላማ ተጠራሁ
Azad From Iraq Kurdistan
ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ
እኔ የተወለድሁትና ያደግሁት በሰሜን ኢራቅ ከመካከለኛ መደብ የኩርዲሽ ቤተሰብ ውስጥ ነው፡፡ እናቴ የሞተችው የአራት ዓመት ልጅ ሆኜ ሲሆን አባቴ ድጋሚ ለማግባት ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ እንደማንኛም ጥሩ አባት በሚገባ በመንከባከብ እና በመውደድ አሳድጎኛል፡፡
አባቴም ስለ እስልምና ትምህርቴ እጅግ በጣም ያስብ ነበር፡፡ እሱም የአረብኛ ፊደሎችን፣ ቁርአንንና የእስልምና ሕግን ገና ከትንሽነቴ ጀምሮም ያስተምረኝ ነበር፡፡ እሱም እጅግ ግሩም ድምፅ ነበረውና እናም ማታ - ማታ ከመተኛታችን በፊት ድምፁን ከፍ አድርጎ ቁርአንን ያነብብ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ባይገባኝ ለእኔ ልዩ ደስታን ይሰጠኝ ነበር፡፡ ከሞተ በኋላ ቆይቶም እንኳን መንፈሳነትን በምፈልግበት ጊዜ ሁሉ የእሱን ድምፅ አስብ እና እገምት ነበር፡፡ ከስድስት ዓመት ዕድሜዬ ጀምሮ ቁርኣንንም ማንበብ ችዬ ነበር፣ እንዲሁም ረመዳንን መፆምና መፀለይን ደግሞ በዘጠኝ ዓመት ዕድሜዬ ጀምሬ ነበር፡፡
በክረምትም የእረፍት ጊዜዎች በቅርብ ወዳለው መስጊድ በመሄድ ስለ ቁርዓን መማርን ቀጠልኩኝ እንዲሁም ቁርአንን እንዴት መተረጎም እንደሚቻል፣ ስለ መሐመድና ስለ ካሊፋቶች ሕይወትም መማር ቀጠልኩኝ፡፡ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ በነበርኩበት ጊዜ የእስልምና ሞደሬት ፓለቲካል ፓርቲ ከሆነ የተማሪዎች ቡድን ጋር ተቀላቀልኩኝ፡፡ በፓርቲውም ሳምንታዊ ተከታታይ ስብሰባ ነበረን በስብሰባውም የእስልምናን መንገድና እንዴትም ንቁ የእስላም ተማሪ ስለምንሆንበት ሁኔታ እንወያይ ነበር፡፡ በመካከሉም እኔ የእስልምናን ሕጎችን መማሬን ቀጠልኩኝ፣ በተጨማሪም ቁርአንን በትክክለኛው መንገድ እንዴት ማንበብ እንደሚቻል፣ የመሐመድን ሕይወት ሐዲትን (ሲራን) እና ደግሞም የአረብኛን ሰዋስውን (ናሁን)፡፡ ከከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም በተመረቅሁበት ጊዜ የፓርቲው ውስጥ ሙሉ አባል ሆኜ ነበር፡፡ በ18 ዓመቴም ወደ ኮሌጅ ገብቼ ነበር፡፡ ዩኒቨርሲቲው የነበረውም በሌላ ከተማ ነበር፡፡ እዚያም በእስልምና ፓርቲው ውስጥ አባላት የነበሩትን ብዙ ተማሪዎችን መተዋወቅ ጀመርኩኝ፡፡
በዚህም ወቅት ብዙ ጥያቄዎች ወደ አዕምሮዬ መምጣት ጀመሩ ለእነዚህም መልስ አልነበረኝም ለምሳሌም ያህል ‹የሕይወት ዓላማ ምንድነው?›፣ ‹ለምንድነው የእግዚአብሔርን ሕግ የምንከተለውና የምናመልከው?›፡፡ የሚሉ ነበሩበት ነገር ግን እንደሚከተሉት ያሉት መልሶች ማለትም ‹እኔ ጅኒዎችንና ሰዎችን የፈጠርኩት እንዲያመልኩኝ ነው› የሚለው 51.57 ሊያረካኝ አልቻለም፡፡ እኔም ከእዚህ የበለጠ ሌላ ዓላማ እንዳለ ገብቶኝ ነበር ይህም ከባርያና ከጌታ ዓይነት አምልኮ ግንኙነት የበለጠ ዓላማ እንዳለ ገብቶኝ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዙሪያዬ በየዕለቱ በማያቸው እውነተኛ ነገሮች እረበሽም ነበር፡፡ በታሪክ መጻሕፍትም እረበሽ ነበር ለምሳሌም የመሐመድ ሕይወትና ባህርይ እንደዚሁም አሁን እንደምናየው ያለው ዓመፅ እና በቁርኣንና በእስልምና ታሪክ ውስጥ እንደምናየው ዓመፅም ጨምሮ ይረብሸኝ ነበር፡፡
በመጀመሪያውም የኮሌጅ ዓመት ውስጥ በእስልምና ላይ ያለኝን እምነቴን ጣልኩኝ፡፡ ከዚያም በንቁ ሁኔታ ለጥያቄዎቼ መልስ ፍለጋዬን ተግቼ ጀመርኩኝ፡፡ በመጀመሪያም እምነታቸውን ለማካፈል እጅግ በጣም ጠንቃቆች በነበሩት በኢራቅ ክርስትያኖች መካከል፣ ከዚያም በየዚዲዎች መካከል ማለትም የጥንታዊ የኩርድሽ ሃይማኖት ተከታዮች በሆኑት መካከል ከዚያም በኤቲዝም (በክህደት) ውስጥ ሁሉ ፍለጋዬን ቀጠልኩኝ፡፡ ይሁን እንጂ እኔ ብዙውን ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ነበረኝ፣ እሱ እንዳለ አውቃለሁ ነገር ግን ወደ እሱ የሚወስደውን መንገድ አላውቀውም ወይንም አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰው ከእሱ ጋር መገናኘትም ያለበት መሆኑን አላውቅም ነበር፡፡
ከዓመታት በኋላ አንድ ቀን ዋልተርን አገኘሁት እሱም በስድሳዎቹ ዕድሜው ውስጥ ነበር፡፡ ከእሱም ጋር ለአንድ ሰዓት ያህል ስለ ፖለቲካዎች አወራን፣ ስለመካከለኛው ምስራቅ፣ ስለ አሜሪካን፣ ስለታሪክ፣ ስለሃይማኖት እና ስለ እግዚአብሔርም አወራን፡፡ ለመጀመሪያም ጊዜ እኔ ባህላዊ ክርስትያን ሳልሆን በኢየሱስ ማመን እንደምችል ሰማሁኝ እንዲሁም እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ከእርሱ ጋር አብሮት እንዲሆንና ከእርሱ ጋር ህብረት እንዲኖረው እንደሆነ ዝም ብሎም ለማምለክ ብቻ እንዳልሆነ ሰማሁኝ፡፡ እኛ ዓመፀኞችም ልጆች ብንሆን እግዚአብሔር አባታችን እንደሆነ እንዲሁም እንደሚወደን ሰማሁኝ፡፡ በጣምም በሚያስገርም ሁኔታ ከአዳም ጀምሮ እስከ ኢየሱስ ድረስ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች በሙሉ እንደተያያዙና የሁሉም ፍሬ ሐሳብ ጭብጥ ታሪክ ያለውና ትኩረቱም ስለ አዳኙ ኢየሱስ እንደሆነ ሰማሁኝ፡፡ ይህን የመጨረሻውን ሐሳብ በጣም አስገራሚ ሆኖ አገኘሁት ምክንያቱም በቁርአን ውስጥ ካለው የእኔ እውቀት የተነሳ ነው፡፡
ዋልተርን ለሁለት ወራቶች ያህል በድጋሚ አላየሁትም፣ እንደገና እንዳነጋግረው የስሜት ግፊት እስካደረብኝ ድረስ እንዲያውም ወደ መርሳት አካባቢ ነበርኩኝ፡፡ እሱንም መፈላለጌን ጀመርኩ በመጨረሻም የኢ-ሜል አድራሻውን አገኘሁኝ፡፡ ኢ-ሜል አደረግሁለት እሱም መልሶ ኢ-ሜል አደረገልኝ፡፡ በመጨረሻም ለመገናኘት ወሰንንና በጥቂት ሳምንት ውስጥ በሳምንት መጨረሻ ላይ መገናኘት ቻልን፡፡
(የበለጠ ሊረዳኝ የሚችልን) መጸሐፍ ስለማንበብ በጠየቅሁትም ጊዜ ይሰጠኛል ብዬ የጠበቅሁት በተለይም ወደ ክርስትያንነት ለተለወጠ ሙስሊም ወይንም ኩርድ የተጻፈ መጽሐፍን ነበር፣ ነገር ግን የመከረኝ መጽሐፍ ቅዱስን እንዳነብብ ነበር፡፡ እኔም በጥንታዊ መጽሐፍ እንደማምን አድርጎ እኔን በመገመቱ ተደንቄ ነበር፣ ለማንኛውም ሐሳቡን ተቀበልኩኝና መጽሐፍ ቅዱስን ማንበቤን ቀጠልኩኝ፣ የጀመርኩትም ከዮሐንስ ወንጌል ነበር፡፡ የመጀመሪያዎቹም ቃላት ከዚህ በፊት ከሰማኋቸው ነገሮች ሁሉ በጣም የተለዩ ነበሩ፡፡
‹በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።› ዮሐንስ 1.1-4፡፡
ማንበቤን ቀጠልኩበት፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ በማነብበት ጊዜ ግን ከዚህ በፊት ባልነበረኝ የአዕምሮ ስሜት ውስጥ ገብቼ ነበር፣ ያም ሙሉ ለሙሉ አሳቢ የመሆንና መንፈሳዊነትን ነበር፡፡ በሚቀጥሉትም ጥቂት ሳምንታት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን ከማንበብ በስቀር ምንም ሌላ ነገርን አላደርግም ነበር፡፡ ለጥያቄዎቼም ሁሉ መልስ የሚሆንን ነገር አገኘሁኝ፡፡ በሕይወቴም ለመጀመሪያ ጊዜ ከመጀመሪያው ጀምሮ እስካሁን ያለውን የሰውን ልጅ ታሪክ ተረዳሁኝ እሱም በአንድና ብቸኛ ዋና ሐሳብ ውስጥ ነው፣ ያም ዋና ሐሳብ፡- ኢየሱስ የሰው ልጅ አዳኝ በሚለው ውስጥ መኖሩን ነው፡፡
ከዕለታት አንድ ቀንም በሌላ ከተማ ውስጥ ከምትኖረው እህቴ ዘንድ የስልክ ጥሪን ተቀበልኩኝ፡፡ እሷም ወደ እርሷ ጋ እንድሄድ ፈልጋ ነበር፡፡ ወደ እሷም ለመሄድ ወሰንኩኝ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን ይዤ ለመሄድ እንደማልችል አውቅ ነበር፣ ምክንያቱም በባስ እሄድ ስለነበር እና እጅግ ብዙ ፍተሻዎች በየመንገዱ ኬላዎች ላይ ስለነበሩ ነው፡፡ እኔም የሰጋሁት መጽሐፍ ቅዱሱን ያገኙትና ችግር ውስጥ እገባለሁኝ ብዬ ነበር፡፡ እህቴም እርጉዝ ስለነበረችና ደግሞም ታማ ስለነበር ቢያንስ ለአንድ ሳምንት ያህል እዚያ መቆየት አለብኝ፡፡ እዚያም እያለሁ የመጽሐፍ ቅዱስን አንዲት ጥቅስ እንኳን ለማግኘት ጓጉቼ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት (ኦን ላየን) እንዳለ ወደ አዕምሮዬ አልመጣልኝም ነበር፡፡ አንድ አርብ ምሽት ላይ አንድ ኢ-ሜል መልእክት ከዋልተር እንዳለኝ ተገነዘብኩ፡፡ መልእክቱንም ከፈትሁት፣ እሱም ከሌሎቹ የተለየ ነበር፣ ያየሁትም የሚከተለውን ነው፡-
‹እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል። ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው። ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።› መዝሙር 23.1-6፡፡
ቀሪውንም ምሽት እነዚህን ጥቅሶች ደግሜ - ደጋግሜ በማንበብ አሳለፍኩት፡፡ ከደስታም የተነሳ እና እነዚህ ጥቅሶች ከሚሰጡት ዋስትና የተነሳ ከአይኔ እንባ ይፈስ ነበር፡፡ የተኛሁበትን ጊዜ በትክክል ምን ያህል እንደሄደ አላወቅሁትም፣ በትክክል የማውቀው ግን ስነቃ ጠዋት ሆኖ እንደነበረ ነው፡፡ ነገር ግን ቀኑ ቅዳሜ ሳይሆን እሁድ ነበር፣ ይሁን እንጂ አሁንም መዝሙር 23 በጆሮዬ ላይ ይደውል ነበር፡፡ እህቴም ሆኑ የእህቴ ባል ለምን ያንን ያህል እንደተኛሁኝ አልጠየቁኝም፡፡ እኔም ቅዳሜን ቀኑን ሙሉ ተኝቼ የነበረ መሆኑን እና አለመሆኑን ማስታወስ እንደማልችል ለመጠየቅ አፍሬ አልጠየቅኋቸውም፡፡ ነገሩ አሁን ምንም አያደርግም ምክንያቱም እኔ ያስተዋልኩት ሞቼ እንደገና መነሳቴን ነው፡፡ (አዲስ ሕይወትን ማግኘቴን ነው)፡፡
በሚቀጥሉትም ጥቂት ቀናት ውስጥ ለጓደኞቼ እኔ እንደተለወጥኩኝና አሁን ሌላ ሰው እንደሆንኩኝ ነገርኳቸው፡፡ እኔም ለጓደኞቼ ስላመንኩት እምነቴ ስናገር በስሜት ውስጥ ሆኜ ነበር፣ ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር ለመስማት ማንም ግድ የማይለው ስለማይለው ተስፋ ቆረጥኩኝ፣ እያንዳንዱም ስለ እግዚአብሔር ለመስማት ጊዜ የሌለው ይመስል ነበር፡፡ የኔ ቤተሰቦችም የኔን መለወጥን ለመካድ መረጡ ምናልባትም በእኔና በእምነታቸው መካከል ያለውን ምርጫ ለመሸከም ስላልቻሉ ነው፡፡
ሰዎች በሚያሳዩት ምላሽም በጣም ቅር ይለኝ ነበር፣ ነገር ግን በኋላ ያስተዋልኩት ነገር ሰዎችን የምንለውጠው እኛ እንዳይደለን ነው፡፡ የሰዎችን ልብ ሊለውጠው የሚችለው የእሱ ፀጋ ብቻ ነው፡፡ እኔም የተረዳሁት ሰዎችን በራሴ ጥረት ለመለወጥ ከመሞከር ይልቅ ስለሰዎች በመፀለይ ብዙ ጊዜ መውሰድ እንዳለብኝ ነው፡፡ ለእነሱ ማሳየት ያለብኝ ምላሼ ፍቅር እና ምህረት እንጂ ፍርድ እንዳልሆነም ተገነዘብሁ፡፡
አዛድ ከኢራቅ
የትርጉም ምንጭ: Called to a higher purpose
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ