የሴቶች ቦታ በንፁህ እስልምና
ክፍል አራትና አምስት - የባል መብቶችና የሴቶች መብቶች
[ክፍል አንድ] [ክፍል ሁለት] [ክፍል ሦስት]
በ M. Rafiqul-Haqq and P. Newton
ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ
1. የባሎች ፍላጎቶች በቅፅበት መሟላት አለባቸው
የወንዶች የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት በጣም አስቸኳይ ስለሆነ ወንዶች ሚስቶቻቸውን በመጠበቅ በፍላጎቶቻቸው ከሚቃጠሉት ይልቅ ምግብ በማንደጃው ላይ ቢቃጠል ይቀላል፡፡ ይህንን ብትቃወም የሰማይ መላክእት በእሷ ላይ ይቆጣሉ፡፡
‹የአላህ ነቢይ እንዲህ አለ፡- ባል ፍላጎቱን እንዲያሟላ ሚስቱን በሚጠራበት ጊዜ፣ ምንም እንኳን በእሳት ላይ ሥራ እየሰራች ቢሆንም ወደ እርሱ ትምጣ› Mishkat al-Masabih, English translation, Book I, Section 'Duties of husband and wife', Hadith No. 61.
(ከዚህ በላይ ያለው ሐዲት ስምምነት የተደረገበት ሲሆን የዚህን ሐዲት እውነተኛነት የሚቃወም የሙስሊም ምሁር የለም)፡፡
‹የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አለ፡- አንድ ወንድ ሚስቱን ወደ አልጋው ሲጠራት እምቢ ብትል ከዚያም ሌሊቱን በንዴት ቢያሳልፍ፣ ጠዋት እስክትነሳ ድረስ መላእክት ሲረግሟት ያድራሉ፡፡› Hadith No. 54 (agreed upon). See also Bukhari, Arabic-English translation, vol. VII, Hadith no. 121.
የወንዶች የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት ከሴቶች በጣም የበለጠ ነው የሚለው ይሄ መረዳት በጥንት ሙስሊሞች ብቻ የታመነ ሳይሆን በዘመናዊው ጊዜም አሁን ባሉ ሙስሊሞችም እንዲሁ የታመነበት ነገር ነው፡፡ ስለዚህም በአሁኑ ጊዜ ያለ አንድ ምሁር እንደሚከተለው ጽፏል፡-
‹በጣም ክቡር የሆነው አላህ የሴትን ሳይኮሎጂያዊና አካላዊ አሰራር ያዘጋጀው የወንድ ፍላጎት በእርሷ እንዲሟላ ነው እንጂ የእሷ ደስታ በወንድ እንዲሟላ አይደለም፡፡ ይህም ብቻ አይደለም እርሷም እራሷ ለእራሷ በስሜቷ ደስታንም ታገኛለች›
Dr. Mohammad Sa'id Ramadan al-Buti, Ela kul Fataten Tu'min be-Allah, Mu'asasat ar_Risalah, Beirut, 1987, Eighth edition, p. 55.
ሌላም የአሁኑ ጊዜ ምሁር እንደሚከተለው ጽፏል፡-
‹የግብረ ስጋ ግንኙነት ድርጊት ነው፣ ሴትም ምንም ድርጊት አታደርግም›
'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al- 'Elmeyah, 1990, vol. 4, p. 7.
ይህንን በተመለከተ ታዋቂው ተንታኝ ቆርቶቢ እንደሚከተለው ብሏል፡-
‹ሴት የተፈጠረችው ወንድ በእርሷ ማረፍ እንዲችል ነው -- ምክንያቱም በእርሷ እርሱ ከግብረ ስጋዊ ማዕበሉ ያርፋልና፡፡ የሴት የግበረ ስጋ ግንኙነት የአካል ብልት የተፈጠረው ለወንድ ነው፡፡ ምክንያቱም ታላቁ አላህ እንዲህ ሲል ተናግሯልና፡ ‹እናንተ ጌታችሁ ለእናንተ የፈጠረላችሁን ሚስቶቻችሁን ትታችኋልን?› The Qur'an, 26:166, Maulvi Mohammad 'Ali's translation. (የአማርኛው ትርጉም ደግሞ ‹ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን?› ይላል)፡፡ አላህ ግልፅ ያደረገው ነገር የሴት አካል ከወንድ የተፈጠረው ለወንድ ሲባል ነው፡፡ ስለዚህም ሴት ባሏ በጠራት ጊዜ ሁሉ እርሱን ማቅረብ አለባት፡፡ ይህንን ብትቃወም ግን እርሷ የምትሆነው ጨቋኝና በከፍተኛ አደጋ ውስጥ ነው፡፡ ቆርጠቢ ቁርአን 30.21 ላይ ያለውን ‹ለናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደነሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ› የሚለውን ሲተነትን፡- ‹የዚህም ብቁ የሆነው ድጋፍ በሳሂህ ሙስሊም ውስጥ ይገኛል እሱም ‹አንድ ወንድ ሚስቱን ወደ አልጋው ሲጠራት እርሷ ከተቃወመች ባሏ እንደገና ደስ እስከሚለው ድረስ በሰማይ የሚገኘው በእርሷ በጣም ይቆጣል› በማለት ጠቅሶ ተናግሯል፡፡
2. ለባል መታዘዝ ለገነት በጣም ቁልፍ ነው፡፡
ሴት ባሏን የማትታዘዝ ከሆነ የእርሷ ማንኛውም ሃይማኖተኝነት ዋጋ ቢስ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ለባሏ ያላት የእርሷ አለመታዘዝ ህገወጥና ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ምሳሌ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለባሏ ያላት የእርሷ ታዛዥነት መንግስተ ሰማይ ለመግባት ዋና ቁልፍ ነገር ነው፣ ይህም በሚከተለው ሐዲት ውስጥ ግልጥ ሆኖ ቀርቧል፡-
‹ፀሎታቸው ተቀባይነት የሌለው፣ ደግነታቸው በላይ በሰማይ የማይወሰድ ሦስት ሰዎች አሉ፣ እነዚህም ከጌታው ዘንድ የኮበለለ ባሪያ ወደ ጌታው እስካልተመለሰ ድረስ፣ ባሏ ያልተደሰተባት ሴት፣ ወደ ትክክለኛ አዕምሮው እስካልተመለሰ ድረስ ጠጪ የሆነ ነው ናቸው› Suyuti, commenting on Q. 4:34, see also Mishkat al-Masabih, English translation, Book I, Hadith No. ii, 74.
‹ባሏ ደስ እየተሰኘባት የሞተች ማንኛዋም ሴት ወደ ገነት ትገባለች› Mishkat al-Masabih, English translation, Book I, Section 'Duties of husband and wife', Hadith No. ii, 60. ‹ነቢዩ አንድ ጊዜ ለአንዲት ሴት እንደሚከተለው ተናገረ፡ ባልሽን እንዴት እንደምትንከባከቢው ተመልከች፣ ምክንያቱም እርሱ ገነትሽ እና ሲዖልሽ ነውና› Suyuti, commenting on Q. 4:34 and Kanz-el-'Ummal, Vol. 22, Hadith No. 868.
3. የባሎች መብቶች ከእግዚአብሔር ናቸው
ሴት ለባሏ የሚኖራት ታዛዥነት መንፈሳዊነቷን አሳይቶ የዘላለም መሄጃዋ ዋስትና ስለሆነ ለእርሷ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ እርሱ (ባሏ) የእርሷ ገነት ወይንም ሲዖል ነው፡፡ ስለዚህም ወንድ ከሴት ጋር ሲነፃፀር እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው (የላቀ) ነው፣ እርሱም የተቀመጠው በመለኮትነት ደረጃ ላይ ነው፡፡ እርሷ ለእርሱ ያላት ምላሽ ወደ አምልኮ የሚደርስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ያ የማይቻል ነው አምልኮ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚገባ ስለሆነ፡፡
መሐመድ አለ፡-
‹እኔ አንድን ሰው በሌላ ሰው ፊት እንዲሰግድ ባዝዝ ኖሮ፣ የማዘው ሴቶች በባሎቻቸው ፊት እንዲሰግዱ ነበር ይህም በአላህ በተደነገገው ወንዶች በሴቶች ላይ ባላቸው መብት ነው› Mishkat al-Masabih, English translation, Section 'Duties of husband and wife', Hadith No. 70. Reported by Abu Dawood, Ahmad, Tirmizi, Ibn Magah and Ibn Haban.፡፡
4. የወንዶች መብቶች ከሴቶች ጡቶች መስዋዕትነት እጅግ በጣም የበለጡ ናቸው፡፡
የወንዶች ደረጃ ከሴቶች በጣም የላቁ ናቸው፣ ያም በሴት በኩል የሚደረግ ማንኛውም መስዋዕትነት አንዲት ሴትን በፍፁም ከወንድ ጋር እንድትስተካከል ሊያደርጋት አይችልም፡፡ በዚህ በእኛም ዘመን እንኳን (1985) የሙስሊም ጸሐፊ አህመድ ዛኬ ቱፋሃ የሚከተለውን ሐዲት በአትኩሮትና በአክብሮት ጠቅሶታል፡-
‹አንዲት ሴት አንዱን ጡቷን እንዲቀቀል እንዲሁም ሌላውን ደግሞ እንዲጠበስ ብትሰጥም እንኳን ለባሏ ያላትን ግዴት ከመወጣት አሁንም የጎደለች ናት፡፡ ከዚህም ሁሉ ባሻገር ባሏን ለዓይን እርግብታ እንኳን ያህል ጊዜ ባትታዘዝ ወደ ሲዖል ዝቅተኛ ቦታ ላይ ትወረወራለች ይህም ተናዝዛ እስካልተመለሰች ድረስ ነው› Tuffaha, Ahmad Zaky, Al-Mar'ah wal- Islam, Dar al-Kitab al-Lubnani, Beirut, first edition, 1985, p. 176. It is also quoted in Al-Musanaf by Abu Bakr Ahmad Ibn 'Abd Allah Ibn Mousa Al-Kanadi who lived 557H., vol. 1 part 2, p. 255፡፡
ይህ ሐዲት በቡካሪ ውስጥ ባይጠቀስም እንኳን በቡካሪ ከተጠቀሱት ከሌሎቹ ጋር በጣም ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡
በጤናማው የቡካሪ አሃዲት ውስጥ እንደተገለፀው ሁሉ ወንድ ሕይወቱን ከሴት ጋር መጋራቱ እጅግ የከበረ መስዋዕትነት ነው፡፡ ምክንያቱም እርሷ በአእምሮዋ፣ በሃይማኖቷ፣ እና በአክብሮቷ ጎዶሎ ሆና እያለ (እርሱ ከእርስዋ ጋር መኖሩ)፡፡ ከእርሷ ጋር ሕይወቱን (ጊዜውን) ማሳለፉ በወንድ በኩል እጅግ በጣም ዝቅ ማለት ነው፡፡ እርሷም ይህንን ውለታ መልሳ ለመክፈል አትችልም፣ ይህም ምንም ዓይነትን መስዋዕትነትን ብታደርግም እንኳን ነው፡፡
በእርግጥ የባል መብቶች እጅግ በጣም ሰፊዎች ናቸው ስለዚህም፡ ‹ከባሏ አፍንጫ ውስጥ የደም መግልና መግል ቢወጣና እርሷ በመላሷ ያንን ብትልሰው አሁንም እርሷ እርሱ በእርሷ ላይ ያለውን መብት ልታሟላው በፍፁም አትችልም›Suyuti, commenting on Q. 4:34፡፡
ይህም ሐዲት አምስት ጊዜ በትልቅ አክብሮት ተደግሟል፣ የተደገመውም በሙስሊም ሊቃውንት ዘንድ ከታላላቆቹ አንዱ እንደሆነ በሚቆጠረው በተንታኙ ኢማም ሱዩቲ ነው፡፡
የሴቶች መብቶች
ሐዲት የወንዶችን በርካታ መብቶች ቢቆጥርም የሴቶች መብቶች ግን በጣም ቀላሎች ናቸው ይህም የሚከተለው ሐዲት እንደሚያሳየው ነው፡-
‹ኦ የአላህ መልእክተኛ! የአንድ ሰው ሚስት ከመካከላችን በባሏ ላይ ምን መብት አላት?› እርሱም መለሰ፡ ‹የራሳችሁን ምግብ ስትወስዱ ለእርሷም መስጠታችሁ ነው፣ ለእራሳችሁም ልብስ ስትለብሱ ለእርሷም ልብስን አልብሷት፣ በጥፊም ስትመቷት ፊቷ ላይ አይሁን፣ ሙልጭ አድርጋችሁ አትስደቧት፣ በቤት ውስጥ ካልሆነ በስተቀር እርሷን ብቻዋን አታውጡአት› Sunan Ibn Magah, Kitab al-Nikah, Hadith No. 1850፡፡
የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-
በንፁህ እስላም ትምህርት ውስጥ ያለው የወንዶችና የሴቶች መብት እጅግ በጣም የተራራቀና መሠረታዊ እንደሆነ ከዚህ በላይ ያለው ጽሑፍ ግልፅ አድርጎታል፡፡ የንፁህ እስልምናም ትምህርት ለወንዶች ስሜታዊና ስጋዊ ደስታ መብት ብቻ የቆመ እና ስለ ሴቶች ስሜት ስጋዊ ደስታና መንፈሳዊ ሁኔታ እንዲሁም ማንኛውም መብቶች ግድ የሌለው መሆኑንም ያሳያል፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው አስተምህሮ ግን የተለየ ነው፡፡ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በፈጠራቸው በእግዚአብሔር ፊት እኩል ናቸው፡፡ ከሴትነት የፆታ ባህርይ በስተቀር የሴት አፈጣጠር ልክ እንደወንድ መሆኑም የሚያሳየው፣ የፆታ ልዩነት መፈጠር ለክቡር ዓላማ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር ተጋብተው በፍቅርና በመረዳዳት በእኩልነት መኖር አለባቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊው የባልና ሚስት ወይንም የወንድና ሴት ትምህርት ሴት ከወንድ ዝቅተኛ አፈጣጠር ያላት የአልጋ ሲሳይ፣ የስሜት ማብረጃ አድርጎ በፍፁም አያቀርባትም፡፡
መጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና በሴቶች ላይ ያለው አመለካከት ሎጂካልና በየትኛውም ትውልድ ውስጥ ላለ የሰው ልጅ አዕምሮ የሚስማማ ነው፡፡ ከፍጥረት ስርዓትም ጋር አብሮ የሚሄድ ነው፡፡ ሌላው አስገራሚ ነገር ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ወንዶች በሴቶች ላይ የበላይነትን እንዲያሳዩም ሆነ እንዲለማመዱ የሚሰጠው ምንም ፍንጭ የሌለው መሆኑ ነው፡፡ ይህ እውነታ መጽሐፍ ቅዱስ በትክክል ከእግዚአብሔር የመጣ ሕያው ቃል መሆኑን ያሳያል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከማንኛውም ባህል ያለፈ፣ ከየትኛውም ዘመን ክልል ያለፈ፣ ከእውቀትም ከሰዋዊ ፍልስፍናም ሁሉ በላይ እውነትን የሚናገር የእግዚአብሔር እውነት ነው፡፡
ስለ ሰው ሕይወትም የሚናገረው እንደዚሁ ትክክል እና እውነት ነው፡፡ ሰው ኃጢአተኛ ነው፣ በኃጢአቱ የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ይገባዋል፡፡ በስራው ለእግዚአብሔር ፍርድ ለመክፈል ሙከራ ቢያደርግ የሚቀበለው የዘላለምን ፍርድና ሲዖል ውስጥ መግባትን ብቻ ነው፡፡
ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ለማዳን ካለው ፍላጎትና ፍቅር የተነሳ የራሱን ፍርድና ቁጣ በልጁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አደረገው፡፡ የዚህም ምክንያቱ ኃጢአተኛው ኃጢአቱን ተናዞ በአዳኙ በጌታ በኢየሱስ በኩል ወደ እግዚአብሔር ቢመጣ የኃጢአቱን ይቅርታና ምህረት በነፃ እንዲያገኝ ነው፡፡
የዚህ ገፅ አዘጋጆችም ዋና ዓላማ አንባቢዎች ይህንን የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንዲችሉ መንገዱን መጠቆምና ወደ ክርስቶስ በንስሐ እንዲመጡ መጋበዝ ነው፡፡ አንባቢ ሆይ በዚህ ገፅ ላይ የሚወጡትን ጽሑፎች በጥንቃቄ አንብብ፣ መጽሐፍ ቅዱስንም አግኝና አንብብ ለራስህም መርምረው፣ እግዚአብሔርም የመዳንን መንገድ እራሱ በመንፈሱ አማካኝነት በቃሉ ውስጥ ይገልጥልሃል ጌታ ይርዳህ አሜን፡፡
የትርጉም ምንጭ: The Place of Women in Pure Islam
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ